👉የመዲናዋ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ም/ኃላፊን ጨምሮ 11 አመራርና ሰራተኞች በፖሊስ ተይዘው ፍርድ ቤት ቀረቡ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ም/ኃላፊን ጨምሮ 11 አመራር እና ሰራተኞች በፖሊስ ተይዘው ፍርድ ቤት ቀረቡ።

1. አቶ ሞሊቶ አባይነህ ኤርቃሎ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ የቀድሞ ም/ኃላፊ፣

2. ኢ/ር ቸርነት አበበ የአደቴ የቦሌ ክ/ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት የቀድሞ ኃላፊ፣

3. ሰለሞን በላይ መኮንን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ የቴክኒክ ጉዳይ ወሳኝ ባለሙያ፣

4. አድማሱ አዳነ ወንድሙ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ የቅሬታ እና አቤቱታ ባለሙያ፣

5. ግዛቸው ሙሉጌታ ደሴ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ ይዞታ ማስተካከል ቡድን መሪ፣

6. ደረጀ ጎሹ ሀይሌ የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የቀድሞ ዋና ሥራ አስፈፃሚ፣

7. አለምፀሃይ ለማ ኪ/ማርያም የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 መሬት ልማትና አስተዳደር የሰነድ አጣሪ ባለሙያ፣

8. ግርማ ተፈራ አያና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ ህግ/ቴክኒክ ጉዳይ ክትትል ዳይሬክተር፣

9. አማኑኤል አለማየሁ ማሞ የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የቴክኒክ ባለሙያ፣

10. ቢኒያም ሀይሉ ገብሬ የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13  የቴክኒክ ባለሙያ እና 11. አቢዮት ጁፋሬ ባይሳ በአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክተር የነበሩ በቁጥጥር ሾር ውለው በፍርድ ቤት ለተጨማሪ ምርመራ የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆ ምርመራው ቀጥሏል።

ግለሰቦቹ ከግበረ አበሮቻቸው ጋር በጥቅም ተመሳጥረው በህዝብና በመንግስት የተሰጣቸውን ኃላፊነት ያለአግባብ በመጠቀም ተጠርጥረዋል።

በዚህም በ2016 ዓ.ም በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው አየር መንገድ አከባቢ የህዝብ እና የመንግስት ይዞታ የሆነውን በ9ኛው መዋቅራዊ ፕላን በዓድዋ ፓርክነት ተይዞ የነበረውን እና በ10ኛ መዋቅራዊ ፕላን በዊንዶው ኦፍ አፍሪካ ልዩ ልዩ የከተማዉ መተንፈሻ አረንጓዴ ስፍራ ፕሮጀክት በከተማ ደረጃ በመናፈሻነት ለህዝብ አገልግሎት የተያዘ እና በመሬት ባንክ ውስጥ ያለን ይዞታ ያለ ህጋዊ ምክንያት ሰነድ አልባ ይዞታ ነው በማለት ለዮርዳኖስ፣ ዘውዲቱ እና ጓደኞቻቸው የሲሚንቶ አከፋፋይ ህብረት ሽርክና ማህበር ለሚባሉት የቦታው ስፋት 2 ሺህ 905 ካ.ሜ ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የቦታው ሊዝ ዋጋ 168 ሚሊየን 724 ሺህ 405 ብር የሚገመትን ጉዳት በማድረስ ከወረዳ፣ ክ/ከተማ እና መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ድረስ በጥቅም ተሳስረዉ ስልጣንን ያለ አግባብ በመገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረዋል።

በዚህም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበው ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ምርመራው መቀጠሉን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment