👉 ቃብድ
✍️ቃብድ ማለት ተዋዋይ ወገኖች ውላቸው እንዲጸናላቸው ያላቸውን ፍላጎት ለማሳየት እና ሽያጩን ለማረጋገጥ አንዱ ወገን ለሌላኛው የሚሰጠው የማስያዣ ገንዘብ ነው። በኢትዮጵያ የውል ሕግ ሥርዓት ውስጥ ቃብድ ከመደበኛ የውል አፈጻጸም ለየት ያሉ የሕግ ውጤቶች አሉት።
1. የቃብድ የሕግ ውጤት በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 1885
እንደ ፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 1885(1) እና (2) ድንጋጌ፣ በቃብድ የታሰረ የሽያጭ ውል ከሌሎች ውሎች የሚለየው በሚከተሉት ነጥቦች ነው፦
ተቃራኒ ስምምነት እስካልተደረገ ድረስ፣ ቃብድ የሰጠው ወገን የሰጠውን ቃብድ በመተው፣ ቃብድ የተቀበለው ወገን ደግሞ የተቀበለውን ቃብድ እጥፍ አድርጎ በመመለስ ውሉን በፈቃዳቸው ማፍረስ ይችላሉ።
በቃብድ የታሰረ ውል እንደ ሌሎች መደበኛ ውሎች በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1776 መሠረት በግዴታ እንዲፈጸም በሕግ አይገደድም።
ይልቁንም ተዋዋዮቹ ቃብዱን በመተው ወይም እጥፍ በመመለስ ከውሉ የመውጣት የመውጫ ቀዳዳ ይሰጣቸዋል።
የቅድመ ክፍያ እና የቃብድ ልዩነት
👇👇👇✍️✍️✍️ተከራካሪዎች የከፈሉት ገንዘብ ቃብድ ሳይሆን ለሽያጭ ዋጋው ማሟያ የተደረገ የቅድመ ክፍያ ከሆነ፣ የቃብድ ሕግ እጥፍ መመለስ ወይም ትቶ መቅረት ተፈጻሚ አይሆንም።
ቃብድ ለተዋዋይ ወገኖች ውሉን የመተው መብት የሚሰጥ ቢሆንም፣ የሚከፈለው ገንዘብ ቃብድ መሆኑንም ወይም የቅድመ ክፍያ መሆኑ በግልጽ መታወቅ አለበት።
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
ሚኪያስ መላክ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service