👉ስለ (Isolated / Pad Footing) ግንባታ ሙሉ እና ዝርዝር መረጃ!
🌟Isolated Footing / Pad Footing በህንፃ ግንባታ ላይ በጣም የተለመደና በስፋት ጥቅም ላይ የሚውል የጥልቀት ዝቅተኛ መሰረት (Shallow Foundation) አይነት ነው።
☄ዋና ዓላማውም የእያንዳንዱን ዓምድ (Column) ጭነት ለብቻው ወደ ታችኛው አፈር ማስተላለፍ ነው።
📌 1. Isolated መሰረት መቼ ጥቅም ላይ ይውላል?
🔹 ጥሩ የአፈር የመሸከም አቅም ሲኖር፦
የመሬቱ አፈር የመሸከም አቅም (Safe Bearing Capacity of Soil) ከፍተኛ ወይም አጥጋቢ በሚሆንበት ጊዜ።
🔹 የአዕማድ እርቀት ሰፊ ሲሆን፦
በአዕማድ መካከል ያለው ርቀት ሰፊ ሆኖ የመሰረት ብረቶች እርስ በእርስ የማይደራረቡ ከሆነ።
🔹 ዝቅተኛ እና መካከለኛ ህንፃዎች ላይ፦
ለቪላዎች፣ ለመኖሪያ ቤቶች (G+0, G+1, G+2) እና ዝቅተኛ ጭነት ላላቸው ህንፃዎች በጣም ኢኮኖሚያዊ የመሰረት አማራጭ ሊሆን ይችላል።
📌 2. በሳይት ላይ Isolated Footing የሚሰራበት ቅደም ተከተል (Step-by-Step Construction Process)
1️⃣ Excavation – የመሰረት ቁፋሮ
• በዲዛይኑ መሰረት የመሰረቱ ስፋትና ጥልቀት ተለክቶ ይቆፈራል።
• ቁፋሮው ከተጠናቀቀ በኋላ የአፈሩ የታችኛው ክፍል በደንብ ይደቀደቃል (Compacted Bottom)።
2️⃣ Lean Concrete / Blinding Concrete – የብላይንዲንግ ኮንክሪት
• የብረት አፅሙ ከቆሻሻና ከአፈር ጋር እንዳይገናኝ ከ 5–10 cm ውፍረት ያለው ዝቅተኛ የኮንክሪት ጥንካሬ ያለው (C-15/C-20) ቀጭን ኮንክሪት ይፈሳል።
3️⃣ Reinforcement Placement – የብረት ዝርጋታ
• በዲዛይኑ መሰረት የታችኛው የብረት መረብ (Bottom Rebar Mat) ይዘጋጃል።
• ብረቱ ከአፈር ወይም ከብላይንዲንግ ጋር እንዳይነካካ በቂ የኮንክሪት ከቨር (Concrete Cover ≈ 50 mm) በብሎኬት/Spacer ማሰሪያዎች ይዘጋጃል።
4️⃣ Column Starter Bars Setup – የዓምድ መያዣ ብረቶች
• የዓምዱ ብረቶች ከመሰረቱ ጋር ተያይዘው በ 90° L-hook ታጥፈው ከመሰረቱ ብረት ጋር በቅርበት ይታሰራሉ።
• የዓምዱ መሃል መስመር (Centerline/Gridline) እንዳይዛነፍ በቴዎዶላይት ወይም በሹሩብ ይረጋገጣል።
5️⃣ Formwork Installation – የፎርምወርክ/ሳጥን ስራ
• የመሰረቱ የጎን ፎርምወርክ፣ የእንጨት ወይም የብረት ሳጥን፣ በዲዛይኑ ልክ ተሰርቶ በጎን በኩል በጥንቃቄ ይደገፋል።
6️⃣ Concrete Pouring & Compaction – ኮንክሪት ማፍሰስና ማደቅደቅ
• የተዘጋጀው ስትራክቸራል ኮንክሪት (C-25 / C-30) ይፈሳል።
• በኮንክሪቱ ውስጥ አየርና ባዶ ቦታ (Honeycombing/Cavities) እንዳይቀር በቪብሬተር (Vibrator) በትክክል ይደቀደቃል።
⚠️ 3. ለጥራት ቁጥጥር (Quality Control) የሚረዱ ዋና ዋና የሳይት ቲፖች
🔹 Curing – ውሃ ማጠጣት፦
ኮንክሪት ከተፈሰሰ በኋላ በቂ የCuring ሂደት ማድረግ የኮንክሪቱን ጥንካሬና ጥራት ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው።
🔹 Starter Bar Lapping፦
ወደ ላይ የሚወጡት የዓምድ መያዣ ብረቶች በቂ የመቀጠያ እርዝመት (Lap Length ≈ 40d–50d) ማሟላታቸውን ማረጋገጥ።
🔹 Backfilling – የአፈር ድቅደቃ፦
መሰረቱ በቂ ጥንካሬ ካገኘ በኋላ በዙሪያው የሚሞላው አፈር በጥሩ Selected Material በየ 15–20 cm ንብርብር እየተደቀደቀ (Compacted in Layers) መሞላት አለበት።
🏗️ በመጨረሻ፦ Isolated / Pad Footing ቀላል የሚመስል ቢሆንም፣ የመሰረቱ ስፋት፣ ጥልቀት፣ የብረት ዝርጋታ፣ Concrete Cover፣ Column Starter Bars እና Concrete Quality በዲዛይኑና በሳይት መመሪያው መሰረት በጥንቃቄ መፈተሽ አለባቸው።
👉የ Isolated Footing ዲዛይን ለማረግ የሚረዳ እንዲሁም ስራቹ የሚያቀልላቹ ምርጥ Excel ፋይል ከፈለጉ ከታች ባለው ሊንክ አውርደው ይጠቀሙ
👇https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a5f6b3b1c816_etconp