#Dexamethasone

“ዴክሳሜታሰን” የተባለው መድሃኒት በኮሮና ቫይረስ በፅኑ የታመሙትን ሰዎች ህይወት ለመታገድ እንደሚረዳ የብሪታንያ ተመራማሪዎች ገለፁ።

ሳይንቲስቶቹ በህክምና ላይ ያሉና በቬንትሌተር የሚተነፍሱት ታማሚዎችን የመሞት እድል በሶስት እጥፍ እንደሚቀንስ የገለጹ ሲሆን በኦክስጅን ውስጥ ያሉትን የመሞት ዕድላቸውን በአምስት እጥፍ እንደሚቀንስ ተናግረዋል፡፡

አሁን የተገኘው ይህ መድሃኒት የኮሮና ቫይረስን (ኮቪድ-19) ለማከም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተደረጉ ትልልቅ ሙከራዎች አንዱ መሆኑንም ነው የቢቢሲ ዘገባ የሚያመለክተው፡፡

ተመራማሪዎቹ የኮሮና ቫይረስ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ይህ መድሃኒት ጥቅም ላይ ውሎ ቢሆን ኖሮ የአምስት ሺ ሰዎችን ሕይወት ማትረፍ ይቻል እንደነበርም አስታውቀዋል፡፡

ይህ መድሃኒት (ዴክሳሜታሶን) ዋጋው በጣም አነስተኛ እና ለድሃ ሀገራትም ጭምር በቀላሉ ሊገዙት የሚችሉት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ ፣ አል ዓይን

@TenaET / https://tena.et

9 comments

መ ለ
temesgen new yihem megegnetu
ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ፤ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ፤ መዝሙረ ዳዊት 18:25
እግዚአብሔር ይመስገን እዉነት ከሁነ
How are you doing?
ልቤ ሰው ይወዳል የቀርበኝ ሁሉ ወዳጅ ይመስለኛል!!!!!
እውነት ከሆነ በጣም ደስ ይላልግን ወሬ ሆኖ እዳይቀር
dess yilal ihe madenit lemin beshita hikimna indemiwul bewul bitawok tiru nbre
Fasika Hamza
Thankyou God this is best information God bless you.
Des emile zena new