👉ሳይት ላይ ሁሌ የሚነሳ ጥያቄ አለ፦ "ብረቱን እናጥፈው ወይስ እንቁረጠው?" 🤔

መጀመሪያ ቢም ሲጫን ምን እንደሚሆን እንመልከት። መካከሉ ወደ ታች ይታጠፋል፣ ስለዚህ ከስር ጭናቅ (tension) ይፈጠራል።

ኮንክሪት ደግሞ ጭናቅን አይችልም። ለዚህ ነው ከስር ብረት የምንሰጠው። ድጋፍ (column) አጠገብ ደግሞ ነገሩ ይገለበጣል። እዚያ ከላይ ጭናቅ ይፈጠራል፣ የመቆራረጥ ኃይል (shear) ደግሞ ከፍተኛ ነው።
አሁን ሁለቱን መንገዶች እንያቸው።

🔵 Bend bar፦ ከስር ያለውን ብረት በ45° ወደ ላይ እናጥፈዋለን። በዚህ መንገድ ብረቱ ድጋፍ ላይ ከላይ ብረት ሆኖ ይሠራል፣ ከstirrups ጋር ደግሞ shearን ይቋቋማል። ግን ማጠፍ ድካም አለው፣ ማጠፊያው ከተሳሳተ ደግሞ ጥቅሙ ይጠፋል።
🟢 Cutting bar፦ ብረቱ ከዚያ በኋላ በማያስፈልግበት ቦታ እንቆርጠዋለን፣ ገንዘብም እንቆጥባለን።
ሥራው ቀላል ነው። ግን አንድ ወሳኝ ነገር አለ፦ ብረቱ መቆም ካለበት ቦታ አልፎ በበቂ ርዝመት መቀጠል አለበት። አጭር ካደረግነው ቢሙ ደካማ ይሆናል።

ታዲያ የቱ ይሻላል? እውነቱን ለመናገር ሁለቱም ትክክል ናቸው፣ በመሐንዲሱ ንድፍ ላይ እስከተመሠረቱ ድረስ።

ዛሬ በብዙ ፕሮጀክቶች ቀጥ ያለ ብረት ከstirrups ጋር መጠቀም የተለመደ ነው፣ ምክንያቱም ሳይት ላይ ለመሥራት ቀላል ነው። ስለዚህ "እንዲህ ልማድ ነው" ብለህ ብረት አታጥፍ ወይም አትቁረጥ፤ drawingውን ተመልከት።

      ━━━━━━━━━━━━━━

​​🌐ለተጨማሪ መረጃ እና ሌሎች የኮንስትራክሽን ዘርፍ ዜናዎች የ YouTube ገፃችን ከታች ባለው ሊንክ በመግባት SubScribe አርገው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG
‎
‎@etconp

Comments

Be the first to add a comment