የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
ያለመያዝ እና ያለመከሰስ መብት ከለላ ያላቸው አካላት
🔙
በኢትዮጵያ አሁን ባለው የህግ ማዕቀፍ ካለባቸው ህዝባዊ ሀላፊነት ወይም የሚወክሉትን ህዝብ/ሀገር ጥቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚከተሉት ሰዎች ከባድ ወንጀል ሲፈፅሙ እጅ ከፈንጅ ካልተያዙ ወይም ያለመከሰስ መብታቸው በህግ በቀመጠው አግባብ እስካልተነሳ ድረስ ያለመያዝ እና ያለመከሰስ መብት በህግ ተሰጧቸዋል።
1ኛ. የምክር ቤት አባላት
2ኛ. ዳኞች
3ኛ. የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት
4ኛ. የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች
5ኛ. የምርጫ ቦርድ አባላት
6ኛ. ለምርጫ የተመወገቡ እጩዎች
7ኛ. የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነሮች
ይህ ያለመያዝ እና ያለመከሰስ መብት ከለላ ዋና አላማው እነዚህ አካላትን ከህግ ተጠያቂነት ለማሸሽ ሳይሆን ከአለባቸው ሀላፊነት አንፃር ስራቸውንን ከአስፈፃሚው አካል ያልተገባ ጣልቃ ገብነት ነፃ ሆነው እንዲሰሩ ማድረግን ታሳቢ ያደረገ ነው።
Comments
Be the first to add a comment