👉ቢም በስላብ ውስጥ ቢደበቅስ? Hidden Beam በሳይት ላይ ሲሰራ ማወቅ ያለብህ ወሳኝ ሚስጥር

​📌 በምስሉ ላይ የሚታዩ ዋና ዋና የምህንድስና ነጥቦች፦

​🔹 Hidden/Submerged Beam Placement፦ ቢሙ ከስላቡ ወለል ውፍረት (Slab Thickness) ጋር እኩል ስለሆነ ከስር ለስላሳ/ፍላት ceiling (Flat Ceiling Finish) እንዲኖረን እና የክፍል ውበት እንዳይበላሽ ያደርጋል።
​🔹 Beam Stirrups & Main Rebar፦ የቢሙ ዋና ብረቶች (Top and Bottom Reinforcement) እና የጎን ስቲረፖች (Stirrups) በጥሩ ሁኔታ ተደራጅተው በስላቡ ብረቶች መካከል ገብተዋል።
​🔹 Polythene Sheet (Vapor Barrier)፦ ከብረቱ ስር የፕላስቲክ ንብርብር (Polythene Sheet) ተዘርግቷል፤ ይህም ኮንክሪት በሚፈስበት ጊዜ የሲሚንቶ ውኃ (Slurry) እንዳይሾልምና እርጥበት እንዳያልፍ ይከላከላል።

​⚠️ ለጥራት የሚረዱ የሳይት ማስታወሻዎች፦

1️⃣ Concrete Cover Blocks (የኮንክሪት ከቨር)፦ በብረቱ እና በፕላስቲኩ/ፎርምወርኩ መካከል ቢያንስ 20 mm - 25 mm የኮንክሪት ከቨር ብሎኮች መደረግ አለባቸው፤ አለበለዚያ ብረቱ ከስር ወጥቶ ለዝገት (Corrosion) ይጋለጣል።

2️⃣ Stirrup Spacing (የስቲረፕ ጥግግት)፦ የ Submerged Beam የዲያሜትር/Depth አነስተኛ በመሆኑ፣ የሼር ኃይልን (Shear Force) በበቂ ሁኔታ ለመቋቋም በድጋፎች (Supports/Columns) አቅራቢያ የስቲረፕ ጥግግት (Spacing) በዲዛይኑ መሰረት መጠበቅ አለበት።

​🌐ለተጨማሪ መረጃ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG
‎
‎@etconp

Comments

Be the first to add a comment