ንዲታወቅለትና የተወሰዱት የውርስ ንብረቶች እንዲመለስለት የሚያቀርበው ክስ ነው፡ ፡ ከዚህ መረዳት የሚቻለው
ክሱ ሁለት ነገሮች የሚረጋገጥበት ነው፡፡ የመጀመሪያው የህግ ሁኔታ (status) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የንብረት
መብት ነው፡፡ የመጀመሪያውን ብቻውን ያየን እንደሆነ በቁጥር በፍ/ሕ/ቀ. 996 ሊስተናገድ የሚችል ሲሆን
የወራሽነት ጥያቄ ግን ከዚህም የሚዘል በመሆኑ የንብረት ክርክርም በውስጡ ይይዛል፡፡ የክሱን ውጤትም ተከሳሹ
በእጁ ያለውን ንብረት እንዲመልስ መደረጉ መሆኑ በፍ/ሕ/ቁ. 1001 መመልከቱ ትኩረቱ ንብረት ላይ መሆኑ
ያረጋግጣል፡፡ ስለዚህ እውነተኛ ወራሽ መሆንን ለማረጋገጥና የውርስ ንብረት ለማስለቀቅ የሚቀርብ ክስ ነው፡፡
የይርጋ ጊዜው ቅድመ ሁኔታ ስናይ ይህን ልዩነት ከግምት ያስገባ መሆኑን ለመረዳት ይቻላል፡፡ ክሱ እንዲቀርብ
የተመለከተው ጊዜ መነሻ ከሳሽ መብቱንና የውርስ ንብረቶችቹ በተከሳሹ መያዛቸውን ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡
የክሱ ይዘት ወራሽነት እና ንብረትን የሚመለከት የመሆኑን ያህል ይርጋውም እነዚህን መብቶች ከግምት የሚያስገባ
ነው፡፡ ከሳሽ ስለአንደኛው ፍሬ ነገር (ስለወራሽነት መብቱ እና ስለንብረቱ) እውቀት ኖሮት ስለሌላኛው ላያውቅ
ወይንም ስለሁለቱም ላያውቅ ይችላል፡፡ ስለመብቱ አውቆ ስለንብረቱ ላያውቅ የሚችልበት አጋጣሚ አንዱ
የወራሽነት ምስክር ወረቀት ይዞ ስለንብረቱ ወይም ንብረቱ በማን እጅ እንደተያዘ ላያውቅ ይችላል፤እነዚህ ፍሬ ነገሮች
ለስሌት መነሻ መሆናቸው የተመለከተ ቢሆንም ሕጉ ሟች ከሞተበት ወይም ከሳሽ ስለመብቱ መስራት ከቻለበት ቀን
አንስቶ በአስራአምስት ዓመታት ውስጥ የወራሽነት ክሱን ካላቀረበ ክሱ በይርጋ እንደሚታገድ በንዑስ 2 ደንግጓል፡፡
ስለዚህ የይርጋ ድንጋጌ ይዘትም የሚያወራው ስለምስክር ወረቀቱ ሳይሆን ስለወራሽነት ጥያቄ (petitio
hereditatis) ነው፡፡ ተቃራኒ ውሳኔ በተንጸባረቀባቸው ውሳኔዎች ለወራሽነት የምስክር ወረቀት የተሰጠው ውጤት
የተለያየ ሲሆን የዚህ ማስረጃ መኖር ወራሽ ተደርጎ ከመገመት ባለፈ የንብረት መብት የማይፈጥር በመሆኑ ሰነዱ በህጉ
ከታሰበለት ዓላማ ውጭ ውጤት መስጠት አይቻልም፡፡ በሌላ በኩል የወራሽነት ጥያቄ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ
ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰ/መ/ቁ. 243973 10 በጽንሰ ሐሳብም
ሆነ በውጤት የተለየ በመሆኑና በይዘቱ በተመለከተው አግባብ የሚቀርብ ጥያቄ የጊዜ ገደብ የተቀመጠለት በመሆኑ
የይርጋ ጊዜው ተፈጻሚነት በወራሽነት ጥያቄ ላይ ነው፤ስለሆነም የወራሽነት ማስረጃ መያዝ አለመያዝ ልዩነት
ሳይኖረው በተጠቀሰው የሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ የወራሽነት ጥያቄ ካልቀረበ ክሱ በይርጋ የሚታገድ ይሆናል፡፡
የወራሽነት ጥያቄ በፍ/ሕ/ቁ. 1000 በተመለከተው የጊዜ ገደብ በይርጋ ይታገዳል፡፡ የውርስ ማጣራት ተጠናቆ
ንብረቱ የጋራ ባልሆነበት ሁኔታ የወራሽነት ምስክር ወረቀት በመያዝ ብቻ የፍ/ሕ/ቁ. 1062 መሰረት በማድረግ
ያለጊዜ ገደብ የክፍፍል ጥያቄ ሊነሳ አይችልም የሚል ትርጉም ተሰጥቷል፡፡
በኢትዮጲያ ባለው የማሕበረሰቡ መስተጋብር ቤተሰብ እርስ በእርሱ ከፍተኛ ቁርኝነት ያለው መሆኑ፤ በውጪ ሐገር የሚኖሩ
ውርሱ የሚገባቸው ሰዎች ውርሱን ለመጠየቅ በማይችሉበት ሁኔታ ላይ ሊገኙ የሚችሉበት አጋጣሚ ያለ መሆኑ፤ ከሁለት
አንዱ ወላጆች ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ በተለይም ታላላቅ ወንድሞች እና እህቶች በሕይወት ያለውን አንደኛውን ወላጃቸውን
ውርሱን ለመጠየቅ የሚቸገሩ መሆኑ፤ በተለይም በሕይወት ላለው ወላጅ ክብር ሲባል ውርሱን የማይጠይቁበት በርካታ
አጋጣሚዎች ያሉ መሆኑን፤ ሌሎች ትንንሽ እህት እና ወንድሞቻቸውንም በውርስ ሐብቱ እንዲጠቀሙበት እና እንዲያድጉበት
ሲባል የውርሱን ክፍፍል የማይጠይቁበት ሁኔታ ያለ መሆኑን፤ ይህም በማሕበረሰቡ የዳበረ ልምድ መሆኑ፤ ይህን ልምድ

Comments

Be the first to add a comment