This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👉በኬንያ ናይሮቢ ግንባታ ላይ የነበረ ግዙፍ ህንፃ ተደረመሰ

🇰🇪🏢 በናይሮቢ ኢስትሌይ አካባቢ ግንባታ ላይ የነበረ ባለ ብዙ ወለሎች ህንፃ በድንገት ተደርምሶ፤ በግንባታው ላይ የነበሩ ሠራተኞች እና እግረኞች በህንፃው ፍርስራሽ ስር ተቀብረዋል በሚል ስጋት የነፍስ አድን ሥራ በከፍተኛ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል።

አደጋው ከቀኑ 7:00 ሰዓት ገደማ የደረሰ ሲሆን በቦታው የነበሩ ሰዎች መንገድ በመዝጋታቸውና ነፍስ አድን አካላትን በማወካቸው ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ በመጠቀም ሰዎችን ለመበተን መገደዱ ተገልጿል።

🚨 የአደጋው መንስኤና በስፍራው የተቀበሩ ሰዎች ስለመኖራቸው እስካሁን የታወቀ ነገር ባይኖርም፤ የናይሮቢ ፖሊስ መረጃዎችን በማጣራት ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

18 ወለሎች የደረሰው የዚህ ግንባታው ያልተጠናቀቀ ህንፃ የታችኛው ክፍሎች፤ ቀድመው አገልግሎት ላይ ውለው እንደነበር የዓይን እማኞች ተናግረዋል።

📹አደጋውን ያሳያል የተባለ ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኘ ቪዲዮ።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment