👉የቢሾፍቱ አየር ማረፊያን ከነባሩ የቦሌ አየር ማረፊያ ጋር የሚያገናኝ የ38 ኪሎሜትር የፍጥነት መንገድ እንደሚገነባ ተነገረ

🛬 ከአዲሱ አየር ማረፊያ ወደ ቦሌ የሚገነባው የፍጥነት መንገድ በእያንዳንዱ አቅጣጫ ስድስት፣ በድምሩ 12 ተሽከርካሪዎችን እንደሚያስተናግድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናግረዋል።

🛣 የፍጥነት መንገዱ የአረንጓዴ አሻራ ያሉት፤ በዙርያው ሙሉ በሙሉ አርንጓዴ መልክዐ ምድር የሚታይበት እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአዲሱ አየር ማረፊያ ግንባታ ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ጠቁመዋል።

🚆በተጨማሪም 38 ኪሎሜትር የሚጠጋ በሰዓት ከ120 እስከ 200 ኪሎሜትር ፍጥነት የመጓዝ አቅም ያለው የባቡር መስመር በሀገር በቀል ኩባንያዎች እንደሚገነባ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

@etconp

Comments

Be the first to add a comment