👉በኢንዶኔዥያ በግንባታ ላይ እያለ የተደረመሰ ትምህርት ቤት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 54 ደረሰ

🚧በኢንዶኔዥያ ትምህርት ቤት መደርመስ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 54 መድረሱን ባለሥልጣናቱ ገልፀዋል፣ የነፍስ አድን ሠራተኞች አሁንም ከ12 በላይ የጠፉ ሰዎችን ፍለጋ ላይ ይገኛሉ።

⚡️በምስራቅ ጃቫ በሚገኘው በአልኮዚኒ ኢስላሚክ አዳሪ ትምህርት ቤት ባለፈው ሳምንት ሰኞ በግንባታ ላይ እያለ የተደረመሰ ሲሆን በወቅቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ለጸሎት ተሰብስበው ነበር።

⏺የኢንዶኔዢያ የአደጋ መከላከል ኤጀንሲ በዚህ አመት በሀገሪቱ የደረሰው አስከፊ አደጋ ነው ሲል ሰይሟል።

⏺በፍርስራሹ ውስጥ የሚገኙ 13 ተጎጂዎችን የማፈላለግ ስራውን የነፍስ አድን ሰራተኞች ለማጠናቀቅ በትግል ላይ ይገኛሉ፡

⏺አሁንም መርማሪዎች የህንጻዉን መደርመስ መንስኤ እያጣራ ነው።

⏺አንዳንድ ባለስልጣናት ባለ ሁለት ፎቅ ሕንፃው የተደረመሰበት ምክንያት መሠረቱ ያልተረጋጋ በመሆኑ የተነሳ ነው ብለዋል።

🏷"በ2025 ከተከሰቱት አደጋዎች ውስጥ በተፈጥሮም ይሁን በሰዉ ሰራሽ ከተከሰቱት የአሁኑን ያህል የሞቱ ተጎጂዎች የሉም" ሲሉ የአደጋ መከላከል ኤጀንሲ ምክትል የሆኑት ቡዲ ኢራዋን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።

❇️ቢያንስ ሁለት ሰዎች ከፍርስራሹ በህይወት ቢወጡም በሆስፒታል ውስጥ ግን ህይወታቸዉ አልፏል፡፡

@etcono

Comments

Be the first to add a comment