👉ለኮንክሪት ጥንካሬና ጥራት ተብለው ስለሚመረቱት ኬሚካሎችና የጥራት ጉድለት ማን ተጠያቂ ይሁን?

በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ በፍጥነት እያደገ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ፣ የኮንክሪትን ባህሪ ለማሻሻል የሚረዱ የኬሚካል አድሚክቸሮች (Admixtures) አጠቃቀም ወሳኝ ደረጃ ላይ ደርሷል።

እነዚህ ኬሚካሎች የኮንክሪትን ጥንካሬ፣ ፈሳሽነት እና የመቆየት አቅም ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ የማሳደር አቅም አላቸው። ይሁን እንጂ፣ በአገር ውስጥ ገበያ ላይ የሚቀርቡ ምርቶች ጥራት ወጥ አለመሆን እና የቁጥጥር ስርዓቱ ክፍተቶች በህንጻዎች እና በመሰረተ ልማቶች ደህንነት ላይ ስጋት እየፈጠሩ ይገኛሉ።

ይህ ሰነድ በአድሚክቸር አቅርቦት ሂደት ውስጥ ሊወሰዱ የሚገባቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች፣ የሚጠበቁ ቴክኒካዊ ሰነዶችን እና የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ (ESA) የሚያስቀምጣቸውን መስፈርቶች በዝርዝር ያብራራል።

ዋና ዓላማውም በግንባታ ሂደት ላይ የሚሳተፉ አካላት ከጥራት ጉድለት ጋር ተያይዞ ከሚመጣ ኪሳራ ራሳቸውን እንዲከላከሉ ሙያዊ መረጃ መስጠት ነው።

1. የተሟላ ቴክኒካዊ ሰነዶች እና የምርመራ ምስክር ወረቀቶች
እያንዳንዱ አድሚክቸር የሚከተሉትን ሰነዶች ማካተት ይኖርበታል፦

•  የምርት መረጃ ዝርዝር (Product Data Sheet - PDS)

•  የቁስ ደህንነት መረጃ ዝርዝር (Material Safety Data Sheet - MSDS)

•  የላቦራቶሪ ምርመራ ሪፖርቶች፦

የኮንክሪት ጥንካሬ ውጤት (Compressive strength results)፣

የመድረቂያ ጊዜ (Setting time)፣

የውሃ ቅነሳ መጠን (%)(water reduction %)፤ እና

ከሲሚንቶ ጋር ያለው ተስማሚነት (compatibility with cement)።

•  እነዚህ ምርመራዎች እንደ ASTM C494 ያሉ ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን መከተል አለባቸው።

የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ / ስጋት

•  አንዳንድ የአገር ውስጥ አቅራቢዎች ያልተሟሉ ወይም ጠቅላላ የሆኑ መረጃዎችን ብቻ ያቀርባሉ።

•  ለእያንዳንዱ የምርት ዙር (Batch-specific) የተሰራ የምስክር ወረቀት እጥረት አለ።

•  አንዳንድ ሰነዶች ከውጭ አገር ምርቶች የተቀዱ እንጂ በአገር ውስጥ የተሞከሩ አይደሉም።

ሊጠየቁ የሚገቡ ግዴታዎች

•  “እውቅና ካላቸው ላቦራቶሪዎች የተሰጠ፣ የተሟላ እና ለእያንዳንዱ የምርት ዙር የተዘጋጀ የምርመራ ምስክር ወረቀት ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ።”

•  “ሰነዶች የምርመራ ዘዴውን፣ ቀኑን እና የመረመረውን ላቦራቶሪ በግልጽ ማሳየት አለባቸው።”

2. በገበያ ላይ ካሉ ምርቶች ጋር የሚደረግ የንጽጽር መረጃ
አዲስ አድሚክቸር ከሚከተሉት ጋር መነጻጸር አለበት፦

•  ያለ አድሚክቸር የተሰራ የኮንክሪት ውህድ (Reference mix)

•  በገበያ ላይ ጥራቱ ከተረጋገጠ ምርት (Benchmark) ጋር ያለው ልዩነትና ተመሳሳይነት


        ንጽጽሩ የሚከተሉትን ማካተት አለበት፦

  የፈሳሽነት ቆይታ (Slump retention)፣

  የጥንካሬ እድገት (Compressive strength results) (በ7 እና 28 ቀናት)፣

  የመድረቂያ ጊዜ (Setting time) እና

  የመቆየት አቅም (Durability)።

የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ / ስጋት

አብዛኞቹ የአገር ውስጥ አምራቾች

•  የንጽጽር መረጃ አያቀርቡም።
•  “ከውጭ ከሚገባው ጋር እኩል
ነው” የሚል የቃል መግለጫ ብቻ ይሰጣሉ።

የንጽጽር የሙከራ ውህድ (Trial mix comparison) ባህል ገና አልዳበረም።

ሊጠየቁ የሚገባው ግዴታዎች

•  “አቅራቢው ተቀባይነት ካለው አድሚክቸር ጋር የተደረገ የንጽጽር የሙከራ ውጤት ማቅረብ ይኖርበታል።”

•  “ውሳኔ የሚሰጠው በአምራቹ መግለጫ ላይ ብቻ ሳይሆን በሳይት ላይ በሚደረግ የሙከራ ውጤት ላይ ተመስርቶ መሆን የገባቸዋል።”

3. ተዛማጅ መስፈርቶችን (ASTM, EN, ወዘተ) ማሟላት
የሚጠበቅ አድሚክቸሮች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፦

•  ASTM C494 (main standard for chemical admixtures)

•  ASTM C260 (air entraining)

•  ሌሎች ኧገር አቀፍና እና አለማቀፍ መስፈርቶችን

  እነዚህ መስፈርቶች የአድሚክቸር አይነቶችን (ከA እስከ G) እና የአፈጻጸም ገደቦችን ይወስናሉ።

የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ / ስጋት

•  ኢትዮጵያ የASTM መስፈርቶችን ብትቀበልም፣ አፈጻጸሙ ወጥ አይደለም።

•  ብዙዎቹ የአገር ውስጥ ምርቶች በASTM መመዘኛዎች ሙሉ በሙሉ አይፈተሹም።

•  “መስፈርቱን ያሟላል” የሚለው አባባል በተግባር ሳይረጋገጥ በይፋዊ መግለጫ ላይ ብቻ ይሰፍራል።

ሊጠየቁ የሚገባው ግዴታዎች

•  “አድሚክቸሩ የASTM C494 (ወይም ተመጣጣኝ የEN መስፈርት) ሙሉ በሙሉ ማሟላቱን ማሳየት አለበት።”

•  “መስፈርቱን ማሟላቱ በገለልተኛ ላቦራቶሪ የምርመራ ውጤት መደገፍ አለበት።”

4. የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ (ESA) ምስክር ወረቀት
ምርቱ የሚከተሉት ሊኖሩት ይገባል፦

•  የESA የምስክር ወረቀት ወይም ምዝገባ።

•  የአገር ውስጥ የጥራት ተስማሚነት ግምገማ (Conformity assessment)።

የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ / ስጋት

•  በገበያ ላይ ያሉ አብዛኞቹ አድሚክቸሮች በኢትዮጵያ ደረጃ መዳቢዎች የተመዘገቡ ወይም የተረጋገጡ አይደሉም።

•  አንዳንድ ምርቶች ያለ ESA ጥብቅ ቁጥጥር ወደ ገበያ ይገባሉ።

ሊጠየቁ የሚገባው ግዴታዎች

•  “ከኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ህጋዊ የምስክር ወረቀት ወይም ፈቃድ ያላቸው አድሚክቸሮች ብቻ ተቀባይነት ይኖራቸዋል።”

•  “አቅራቢው ህጋዊ የምስክር ወረቀት እና የምዝገባ ቁጥር ማቅረብ ይኖርበታል።”

5. የጽሁፍ የአፈጻጸም ዋስትና እና የተጠያቂነት ማረጋገጫ (Written performance guarantee and liability confirmation)

አቅራቢው የሚከተሉትን ማቅረብ አለበት፦

•  የጽሁፍ የአፈጻጸም ዋስትና።
•  ለጥንካሬ ጉድለት፣ ለመድረሻ ጊዜ ችግሮች እና ለጥንካሬ መጓደል ተጠያቂነትን የመውሰድ ማረጋገጫ።

የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ / ስጋት

•  ብዙ አቅራቢዎች የጽሁፍ ተጠያቂነት ከመውሰድ ይቆጠባሉ።

•  የቃል ማረጋገጫ ብቻ ይሰጣሉ።

•  ችግር በሚፈጠርበት ጊዜ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እና ክርክሮችን ለመፍታት አስቸጋሪ ይሆናል።

ሊጠየቁ የሚገባው ግዴታዎች

•  “አቅራቢው ለተጠቀሰው የውህድ ዲዛይን (Mix design) የጽሁፍ የአፈጻጸም ዋስትና መስጠት ይኖርበታል።”

•  “ከአድሚክቸሩ ጥራት ጉድለት ጋር ተያይዞ ለሚመጣ ማንኛውም ቴክኒካዊ እና ፋይናንሳዊ ኪሳራ አቅራቢው ሃላፊነቱን ሊወስድ ይገባል።”


ማጠቃለያ

በኢትዮጵያ የአድሚክቸር ምርት እያደገ ቢሆንም፣ በሚከተሉት ምክንያቶች የጥራት ስጋቶች አሉ፦

1.  ደካማ የሰነድ እና የምርመራ ስርዓት።

2.  የንጽጽር ሙከራዎች እጥረት።

3.  የASTM መስፈርቶችን ሙሉ በሙሉ አለመተግበር።

4.  የESA የምስክር ወረቀት አሰጣጥ ወጥ አለመሆን።

5.  የአቅራቢዎች ተጠያቂነት ግልጽ አለመሆን።

ስለሆነም፦ ማንኛውንም አድሚክቸር ከመፍቀዳችን በፊት ጥብቅ የቴክኒክ ሰነዶችን መጠየቅ እና በሳይት ላይ በተግባር ማረጋገጥ የግድ አስፈላጊ ነው።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment