👉አዲስ የግንባታ ፕሮጀክት አካላዊ አፈጻጸም መመዘኛ ሥርዓት ይፋ ሆነ

በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን፣ በኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት እና በሜድሮክ አርክቴክቶችና መሐንዲሶች ትብብር በሐርሞኒ ሆቴል የግንባታ ፕሮጀክት አካላዊ አፈጻጸም አዲስ መመዘኛ ላይ ያተኮረ ሥልጠና ተካሄደ።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር ከሥልጠናው መውጣት በኋላ ባወጣው ማጠቃለያ እንዳስታወቀው፣ አዲሱ ሥርዓት የግንባታ ፕሮጀክቶች አካላዊ አፈጻጸም በግምት ሳይሆን ግልጽ፣ ሊረጋገጥ የሚችልና ወጥ በሆነ መንገድ እንዲለካ የሚያስችል ነው።

​በአዲሱ መመዘኛ መሠረት የሥራ አፈጻጸም በሰው ኃይል እና ማሽን ሰዓት ስሌት (Man-Hour/Machine-Hour Weightage) እንዲሁም በቢ.ኦ.ኪዩ (BOQ) የሥራ መጠን እና ክብደት ላይ ይመሠረታል።

ከዚህም በተጨማሪ የፕሮጀክት አካላዊ አፈጻጸም ከፋይናንሺያል አፈጻጸም ተለይቶ በማስረጃ ተደግፎ መቅረብ እንዳለበት እና የትኛውም የቢ.ኦ.ኪዩ ሥራ መደብ ከ100 በመቶ በላይ ሊመዘገብ እንደማይችል ተመላክቷል።

ከዋናው ቢ.ኦ.ኪዩ በላይ የሚሠሩ ሥራዎች እንደ ልዩነት ወይም የለውጥ ትዕዛዝ (Variation/Change Order) ብቻ መመራት አለባቸው።

​ማህበሩ ተቋራጮች የየወሩን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት፣ የክፍያ ጥያቄዎች እና የጊዜ ሰሌዳ ማሻሻያዎችን በአዲሱ መመዘኛ መሠረት እንዲያዘጋጁና አስፈላጊውን መረጃ በጥንቃቄ እንዲይዙ አሳስቧል።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment