ሥራ ፈትነት እንደሚያስቀጣ የውቃሉ ?
አዋጅ ቁጥር 414/1996 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 477 አደገኛ የሆነ ስራ ፈትነት
1. ማንም ሰው ሙሉ አካል እያለው የተወሰነ መኖሪያ ወይም መደበኛ ስራ (ለኑሮው) አስፈላጊ የሆነ መደበኛ ወይም ጉልህ የሆነ የገቢ ምንጭ የሌለው ሆኖ የስራ ፈትነትን ወይም የመጥፎ አኗኗር አመልን ገንዘብ ለማግኘት ሲል ነቀፌታ ያለበትን መጥፎ ዘዴ አስቦ ልማድ አድርጎ የያዘና በዚሁ ኑሮው ለሕዝብ ደሕንነትና ጸጥታ አደገኛ የሆነ እንደሆነ፡፡
የግል ነፃነትን ከመቀነስ ጋር በሚወሰን የግዴታ ሥራ /አንቀጽ 104/ወይም ከስድስት ወር በማይበልጥ ቀላል እሥራት ይቀጣል ፡፡
2. ጥፋተኛው የጦር መሣርያ ወይም በጠባያቸው ወንጀልን ለመፈጸም የሚያገለግሉ መሣሪያዎች ይዞ የተገኘ እንደሆነ በቀላል እሥራት የሚቀጣ ሲሆን ዛቻን ወይም የማሥገደድ ድርጊትን ወይም በግለሠቦች ላይ የኃይል ድርጊት ወይም የእጅ እልፈት የፈጸመ እንደሆነ ስለወንጀሎች መደራረብ የተመለከተው ድንጋጌ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
3. ሁኔታዎች ሲመዛዘኑ ተገቢሆኖ በታየ ጊዜ ፍ/ቤቱ የነፃነት መቀነስ የጥንቃቄ እርምጃዎችን /አንቀጽ 144/147/ ከዋናው ቅጣት ጋር አጣምሮ ለመወሰን ይችላል፡፡


አሊ ሣፊ (አቃቤ ሕግ)
ሚያዚያ 12/2014 ዓ.ም
ቸር ይግጠመን!!

Comments

Be the first to add a comment