👉በማንኛውም የኮንስትራክሽን ሳይት ላይ፣ የአንድ ኮለም (column) ቱምቢው የተወሰነ ሲኖረው "5 ሚ.ሜ ብቻ እኮ ነው፤ ምንም አያመጣም በልስን ይስተካከላል" የሚለውን የተለመደ አባባል እንሰማለን።
ይህ የ "5 ሚ.ሜ ህግ" በብዙ ባለሙያዎች ዘንድ የተለመደ ነው። ነገር ግን ይህ 5 ሚ.ሜ ከየት መጣ? የህንፃ ኮዱስ በእርግጥ ምን ይላል? እስኪ አብረን እንየው....
በኮንስትራክሽን execution ወቅት በሳይት ላይ የሚፈጠሩ የአሰራር ጉድለቶችን (workmanship errors) ታሳቢ ለማድረግ፣ የEBCS code (EBCS EN 1992-1-1:2013) አንቀጽ 5.2 ለጂኦሜትሪክ መዛባት (geometric imperfection) በdesign stage ታሳቢ እንዲደረግ በግልፅ አስቀምጧል። እውነታው ሲመረመር የሳይቱ "5mm" ህግ የመጣው ከነዚህ የኮድ እሴቶች የመነጨ ነው::
🚥1. የቱምቢ ችግር (Verticality/Plumbness): ኮዱ አንቀጽ 5.2(5) ላይ መሰረታዊ የማጋደል መጠንን/inclination (1/200) በማለት ያስቀምጣል።
ይህ ማለት በየ 1 ሜትር ቁመት 5 ሚ.ሜ ማጋደል በdesign ወቅት ታሳቢ መደረግ አለበት ማለት ነው::
ለምሳሌ የተለመደውን 3 ሜትር ቁመት ያለው ኮለም ብንወስድ፣ Design ሲደረግ ታሳቢ የሚደረገው አጠቃላይ ማጋደል 15 ሚ.ሜ (3000/200) ነው።
በሳይት ላይ የምናገኘው "5mm" ከ 15mm ስለሚያንስ እጅግ በጣም ጥብቅ (Conservative) ሆኗል ማለት ነው so ተቀባይነት አለው ማለት ነው።
🚥2. የሊኛ ችግር (Horizontal Shifting/Eccentricity): ኮዱ አንቀጽ 5.2(7)(a) ላይ braced systems ላሉ ኮለሞች የኤክሴንትሪሲቲ መጠንን (Lo/400) በማለት ያስቀምጣል, lo ማለት የኮለሙ clear height ነው።
ለ 3 ሜትር (3000 ሚ.ሜ) ኮለም፣ የሚፈቀደው የHorizontal Shifting 7.5 ሚ.ሜ (3000/400) ነው።
እዚህም ጋር የሳይቱ የ 5 ሚ.ሜ ልማድ በdesign stage ከታሰበው የ 7.5 ሚ.ሜ ገደብ በታች በመሆኑ ስህተቱን በአስተማማኝ ሁኔታ (safely) ያስተናግደዋል።
እዚህ ጋር ልንገነዘበው የሚገባው ዋና ነጥብ፣ እነዚህ 1/200 እና Lo/400 አሃዞች የሳይት ላይ ስህተት መለኪያ ሳይሆኑ፣ ገና በዲዛይን ደረጃ (Design Stage) በስትራክቸራል መሃንዲሱ ስሌት ውስጥ የገቡ ታሳቢዎች መሆናቸውን እና ከቻልን zero error ካልቻልን ግን ለzero የቀረበ ሥራ እንድንሰራ ነው::
🗂መዛባቱ ትክክለኛውን የኮድ ገደብ (Actual Code Limits) ቢያልፍስ ምን ይፈጠራል??
🌟አንድ ኮለም ከላይ ከተጠቀሱት የኮድ ገደቦች ውጭ ሲያፈነግጥ፣ በኮለሙ ላይ የሚከተሉት ከባድ ስትራክቸራዊ ችግሮች ይፈጠራሉ እነሱንም እንደሚከተሉት አቀርብላችኋለሁ
🚥1. ያልታሰበ የጎንዮሽ ሞመንት መፈጠር (Unintended & Biaxial Bending): ኮለሙ ከሴንተር ላይኑ ሲያፈነግጥ ከላይ የሚመጣው ሸክም (axial load) በቀጥታ በኮሎሙ የክብደት ማዕከል (centroid) ላይ አያርፍም።
ይህ eccentricity በዲዛይን ወቅት ያልታሰበ ተጨማሪ ሞመንት (additional moment) በኮሎሙ ላይ ይፈጥራል(M=N*e)።
ኮሎሙ በሁለቱም አቅጣጫዎች (x እና y) ካጋደለ ደግሞ፣ ስትራክቸሩን ለበለጠ ጫና የሚያጋልጥ የሁለት አቅጣጫ ሞመንት (Biaxial Bending) ይፈጠራል ማለት ነው።
🚥2. የሁለተኛ ደረጃ እና የ P-Delta ተፅዕኖ (Second-Order & P-Delta Effects): መዛባቱ በጨመረ ቁጥር የኮሎሙ የጎንዮሽ ዝንበሌ (Deflection) ይጨምራል። ከላይ የሚያርፈው ሸክም በዚህ ያጋደለ ኮሎም ላይ ሲያርፍ፣ ሸክሙ እና Deflection ተባዝተው ተጨማሪ የሁለተኛ ደረጃ ሞመንት ይፈጥራሉ (P-Delta effect)።
ይህ ተፅዕኖ በተለይ ለቀጫጭን እና ረዣዥም ኮለሞች (slender columns) የኮሎሙን ሸክም የመሸከም አቅም በከፍተኛ ፍጥነት እንዲቀንስ ያደርገዋል።
🚥ሌላኛው የስትራክቸር መጎዳት እና የመሰበር አደጋ (Structural Distress & Failure): በመዛባቱ ምክንያት የተፈጠረው አጠቃላይ ሞመንት ኮለሙ design ከተደረገበት አቅም (design capacity) በላይ ሲሆን፣ በአንድ በኩል ያለው ኮንክሪት መሸርሸር እና መሰንጠቅ (concrete crushing/spalling) ይጀምራል።
▶️በሌላ በኩል ያለው ብረት (reinforcement) ከአቅም በላይ በመወጠር (yielding) ውሎ አድሮ ኮለሙ buckling failure ሊያጋጥመው ይችላል ማለት ነው።
▶️ይህን ከገደብ በላይ የሆነ መዛባት የሚያስከትለውን ከባድ የስትራክቸር አደጋ ከተረዳን "መቻቻል (tolerance) አለ" ብለን በስራችን ላይ ፈፅሞ መዘናጋት የለብንም።
⏺ይልቁንም በሳይት ላይ ስራዎችን ስንሰራም ሆነ ስናሰራ ከፍተኛ ጥንቃቄ እና የጥራት ቁጥጥር በማድረግ፣ እንዲህ አይነት አደገኛ ሁኔታዎች እንዳይፈጠሩ የቻልነውን ሁሉ ማድረግ የሁላችንም የሙያ ግዴታ መሆኑን ላስታውሳቺሁ እወዳለሁ።
🏛የQuantity Surveying እና Building Construction Estimation ከ ሀ አስከ ፐ ችሎታዎን በተግባራዊ ምሳሌዎች የሚያሳድጉበት ምርጥ መፅሐፍ ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱት
👇https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a8dd294cbaa9_etconp