ሰላም ውድ የቴሌግራም ቻናል አባሎቻችን! ከምርጫ ነክ መልዕክቶች ወጣ ብለ ጋብቻንና ፍቺን በተመለከተ አንዳንድ ነጥቦችን ከኢትዮ ሕግ ( https://m.facebook.com/ethiohig/?__tn__=C-R) ሳነብ ካገኘውት ላጋራችሁ ወደድኩኝ።
ጋብቻ በእንደራሴ መፈጸም በመርህ ደረጃ የማይቻል ቢሆንም ከተጋቢዎች አንደኛው ጋብቻውን ለመፈጸም ፈቃዱን በማያሻማ ሁኔታ በመግለጽ በግንባር ለመገኘት የማያስችለው ከባድ ምክንያት ሲያጋጥመው ጉዳዩ ለፍትህ ሚኒስትሩ ቀርቦ ሲረጋገጥ ጋብቻውን በእንደራሴ አማካኝነት መፈጸም እንደሚቻል በግልጽ በተሻሻለው የፌደራል ቤተሰብ ህግ አንቀጽ 12 ተደንግጓል፡፡
በመሆኑም የተሰጠው የውክልና ማስረጃ ይዘት በፍትሐ ብሔር ስነ ስርአት ህግ ቁ.58 እና በፍትሐብሔር ህግ ቁ.2199 ተወካዩ ፍቺን ጨምሮ በማናቸውም ጉዳዮች ወክሎ ለመከራከርም ሆነ ሌላ የህግ ባለሙያ ለመወከል እንደሚችል በውክልና ሰነዱ ላይ በግልጽ የተመለከተ ከሆነ ፍች በዉክልና አይጠየቅም ተብሎ ሊከለከል አይገባም፡፡
ጋብቻ ለመፈጸም በልዩ ሁኔታ በውክልና እንደሚቻል ህጉ እየፈቀደ የፍቺ ጥያቄ ፍርድ ቤት የባልና ሚስትን ክርክር በሚያይበት ጊዜ እንደነገሩ ሁኔታ አስፈላጊ ሁኖ ካገኘው ባልና ሚስቱን በአንድነት ወይም በተናጠል ሲያነጋግር ወይም ጉዳዩን ሲመረምርና ምስክር ሲሰማ በዝግ ችሎት ያስችላል የሚለውን የቤተሰብ ህጉን ድንጋጌ አንቀጽ 110 በመጥቀስ ጋብቻና ፍች በውክልና ሊጠየቅ አይችልም በሚል የሚቀርብ ክርክር ተገቢነት የለዉም፡፡ ምክንያቱም ፍርድ ቤቱ ተጋቢዎችን በአካል የሚያነጋግራቸው አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እንጂ የግድ ማናገር እንዳለበት የሚደነግግ ህግ የለም ::
(ሰበር መ/ቁ.150408 ቅጽ 23.)
ቸር ያሰማን! (15/07/2013 ዓ.ም) ( ኦምኒኤል)

Comments

Be the first to add a comment