👉የፍሳሽ ስርገትና ርጥበትን መከላከል/Damp Prevention/

ክፍል አንድ

አንድ ህንጻ የታሰበለትን የተሟላ አገልግሎት እንዲያስገኝ ከሚያስፈልጉ ፍላጎቶች አንዱ ህንጻው ከማንኛውም በግድግዳ፣በጣሪያና ከመሬት በላይ ወይም ከመሬት ስር በሚኖረው ወለል ከሚመጣ ፍሳሽ ከሚፈጠር ርጥበት/hygroscopic moisture/ የጸዳና ደረቅ መሆኑ ነው።

💧ለርጥበት መከሰት ምክንያቶች/Sources of Dampness/:

1.ከመሬት ውስጥ ወደላይ የሚወጣ ውሃ/Moisture Rising up the wall from Ground/:

2.ግድግዳን ሰርጎ ውስጥ ለውስጥ ወደታች የሚወርድ የዝናብ ውሃ/Rain Travel from wall Tops/

3.በግድግዳ ሰርጎ ግድግዳውን የሚያለዝብ የዝናብ ውሃ/Rain beating against External wall/

4.ጥዘት/Condensation/

5.ሌሎች ምክንያቶች

-ደካማ የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት

-የህንጻ አቀማመጥ አቅጣጫ ልክ ያለመሆን/imperfect orientation/

-በቂ ያልሆነ የጣራ ተዳፋት/imperfect Roof slope/

-የግንባታ ጥራት ችግር........

💧የርጥበት መከሰት የሚያስከትካቸው ችግሮች/Effects of Dampness/

1.ንጽህናው ያልተጠበቀና ጤናን የሚጎዳ ሁኔታን ይፈጥራል፣

2.ለወባ ትንኝ መራባት ምቹ  ምክንያት ይሆናል።

3.ለተጠቃሚዎች ምቾትን የሚነሳ አካባቢ እንዲፈጠር ያደርጋል።

4.የልስን ስራ ላይ መሳሳትና መፈርፈር ምክንያት ይሆናል።

5.እንደቀለምና የቤት ማስዋቢያ ስራዎች ላይ ብልሽት ያስከትላል።

6.የወለልና ግድግዳ ማጠናቀቂ ስራዎች/Damages on floor & wall coverings/

7.ከብረት የተሰሩ የተለያዩ የግድግዳ፣ወለልና ጣሪያ ስራዎች ላይ ዝገት እንዲፈጠር ያደርጋል።

8.እንደ ኤሌክትሪክ ስራዎችና

በአጠቃላይ የህንጻ ደህንነት ላይ አደገኛ ደረጃ ጉዳት እስከማድረስ ችግር ሊፈጥር ይችላል ማለት ነው።

በቀጣይ ክፍል .....

💧የውሃ ስርገትና ርጥበትን የመከላከልያ መንገዶች/Methods of Dampness prevention and water proofing works/

@etconp

Comments

Be the first to add a comment