👉የአዲስ ኮንክሪት ጥሩ ባህርያት /Properties of Fresh Concrete/

➡️ኮንክሪት ለመብላለት/ለመደባለቅ/Mix/፣ ከቦታ ቦታ ለማንቀሳቀስ/to transport/፣ለማስቀመጥ/deposit/ እና ለመጠቅጠቅ/Compact/Vibrate/ ቀላል ወይም ምቹ ሆኖ ሲገኝ ጥሩ ነው።

➡️የእነዚህ ጥምር ውጤት ኮንክሪቱ ከስራ ምቹነቱ ባሻገር ኮንክሪቱ ላይ የመግጠጥ ችግር እንዳይከሰት /resistance to segrigation/ የሚረዳ ይሆናል።

➡️ከላይ የገለፅናቸውን ባህርያት ያሟላ ኮንክሪት «ምቹ»/Workable/ ነው ብለን የምንጠራው ይሆናል። እንዚህን ባህርያት የሚያሟላ መሆኑን የምናተጋግጥበት የስራ ምቹነት/ፅኑነት ምርመራ/ workability test/ Consistancy test ይባላል።

➡️የኮንክሪት workability ላይ ተፅዕኖ ሊያደርሱ የሚችሉ ምክንያቶች ምን ሊሆኑ ይችላሉ?

*1ኛ.የውህድ ምጣኔ ትክክል አለመሆን/Mix ratio/

*⃣2ኛ. የጠጠር ወይም የአሸዋ የግርድፍ መጠናቸው/Gradation/ ወይም ቅርፅ/Shape/ልክ ያለመሆን

➡️የኮንክሪት workability እንዴት ማወቅ እንችላለን?

*በሳይት እና በቤተ ሙከራ ይህን የምናረጋግጥባቸው 4 መንገዶች አሉ።እነዚህም:

➡️1. Slump test
➡️2.Compacting factor test
➡️3.Veebee test እና
➡️4.Vibro workability test ናቸው።

🌟ኮንክሪት ስላምፕ ቴስት/Slump test/Cone test/Sand test/

➡️የኮንክሪት ስላምፕ ቴስት በቀላሉ በሳይት የሚተገበር የፍተሻ አይነት
ሲሆን የኮንክሪትን ለስራ ያለውን ምቹነት (Workability) እና ፅኑእነት
(Consistency) ለመለካት ይጠቅማል።

➡️ኮንክሪት ስላምፕ ቴስት በየእያንዳንዱ የኮንክሪት ሙሌት ስራ ወቅት መሰራት ያለበት ሲሆን በምን ዓይነት የጊዜ ልዩነት ወይም በየስንት መጠን መሰራት እንዳለበት በየኮዱ የሚለያይ ይሆናል።

➡️ስላምፕ ቴስት በቀላል ወጪ የሚሰራ በመሆኑ ተመራጭ የመፈተሻ መንገድ ነው። በዚህ ምክንያት ከ1922GC ጀምሮ እስካሁን አገልግሎት ላይ እየዋለ ይገኛል።

➡️የኮንክሪት ስላምፕ ቴስት ውጤት ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ሁኔታዎች
(Factors influencing slump test result)

*1- ለኮንክሪቱ የተጠቀምናቸው ግብአቶች ባህርይ።

🌟ለምሳሌ: ስነውህድ (ኬሚስትሪ) ቅጥነት ፣ የቁሱ መጠን እና ስርጭት (particle size and distribution) ፣ እርጥበት
፣ የሲሚንቶ ግብአት እና እርጥበት የመያዝ አቅም.

*2- የኬሚካል አድሚክስቸር መጠንና አይነት መስተጋብር.

*3- የኮንክሪቱ አየር የመያዝ አቅም።

*⃣4- ኮንክሪት ማቀላቀያ ማጓጓዣ ቁስ እና ዘዴ

*⃣5- የኮንክሪቱ ሙቀት መጠን /temperature/

*⃣6- የተጠቀምነው የውሃ መጠን

*⃣7- ለፍተሻ የተወሰደበት ግዜ

🌟Slump test ለማድረግ የምንጠቀማቸው እቃዎች ምን ምን ናቸው?

➡️ጉርድ የኮን ቅርፅ/Truncated cone/

*⃣ይህ ቅርፅ ማውጫ 30cm የታችኛው ዲያሜትር 20 cm የላይኛው ዲያሜትር 10cm ዲያሜትር ነው

➡️Plate/መደብ/

*⃣ከብረት የተሰራ 16 mm dia. እና 60 cm ርዝመት ያለው
መጠቅጠቂያ ብረት/Compaction rod/

🌟የስራ ቅደም ተከተሉ እንዴት ነው?

*⃣1ኛ. መጀመርያ የቅርፅ ማውጫ ኮን (mold ) ንፁ መሆን አረጋግጥ ኮንክሪቱ በቀላሉ ከሞልድ እንዲላቀቅ ቅርፅ
ማውጫውን ዘይት መቀባት አለበት።

*⃣2ኛ. ቅርፅ ማውጫውን (mold ) ትልቅ ዲያሜትር ባለው ጫፍ በኩል ወንፊት ባልሆነ ስሃን/plate/ ላይ ማስቀመጥ።

*3ኛ. የቅርፅ ማውጫ (mold) በእኩል 4 layer በኮንክሪት መሙላት።

*⃣4ኛ. እያንዳንዱን የኮንክሪት ሌየር 25 ግዜ በመጠቅጠቂያው ብረት መምታት የአጠቃጠቅ ጉልበታቱ እኩል መሆን አለበት።

*⃣5ኛ. ኮኑ (mold) ከሞላ በኋላ ትንሽ ስፋት ባለው ጫፍ ላይ ያለ ትርፍ ኮንክሪትን በቅርፅ ማስወገድና መለሰን።

*⃣6ኛ. በርጋታ ቅርፅ ማውጫውን
(mold) ወደላይ በመሳብ ከኮንክሪቱ ማለያየት።

*⃣7ኛ. ቀጥሎም ኮንክሪቱ ከቅርፅ ማውጫ (mold) ያለውን የርዝመት ልዩነት መለካት።

🌟ማስታወሻ:

*⃣ሳምፕሉ ከተወሰደ በሁለት ደቂቃ ውስጥ ቴስቱን መከወን አለብን።

🌟ከቴስት በኋላ የምናገኛቸው የውጤት አይነቶች:/Results to be/[

➡️True Slump:

*⃣ይህ ከፍተሻው ምናገኘው ትክክለኛው ልኬት ነው።

🌟ቅርፅ ማውጫው ከኮንክሪቱ ከተለያየ በኋላ ያለው የኮንክሪቱ ቁመት ከቅርፅ ማውጫው አንፃር የምናገኘው ልዩነት ነው።

➡️Zero Slump:

*ዜሮ ስላምፕ ኮንክሪቱ አነስተኛ የውሃና
ሲሚንቶ /water-cement ratio/ያለው መሆኑን ያሳያል።

➡️Collapsed Slump:

*⃣ይህ ከዜሮ ስላምፕ በተለየ
የኮንክሪቱን የውሃና ሲሚንቶ/water-cement ratio/ ምጣኔ ትልቅ መሆን ያሳያል።የኮንክሪቱ የእርጥበት መጠኑ ከፍተኛ በመሆኑ እና High workability mix መሆኑን ያሳየናል።

➡️Shear Slump

*⃣ይህ ደግሞ የፍተሻው ውጤቱ ሙሉ
እንዳልሆነ ይነግረናል።
…………………………………

🌟ከወደፊት ሌሎች የኮንክሪት ለስራ ያለው ምቹነት ላይ ያለውን ደረጃ የምንመዝንባቸው የቴስት ዓይነቶች የምናቀርብ ይሆናል።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment