የ ሪል ስቴት ጉዳይ

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍሊንትስቶንስ ኢንጂነሪንግ አፓርትመንቶች ተሽጠው ለ87 ባለመብቶች እንዲከፈል አዘዘ፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍትሐ ብሔር ምድብ ችሎት፣ ፍሊንትስቶንስ ኢንጂነሪንግ አክሲዮን ማህበር ለ87 ባለመብቶች ያለበትን ዕዳ ለመክፈል፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የሚገኙ ቤቶቹ በጨረታ ተሽጠው ገንዘቡ ለባለመብቶቹ እንዲከፈል ውሳኔ አስተላልፏል።

ትዕዛዙን የተሰጠው ትናንት ህዳር 10 ቀን 2019 ዓ.ም በዋለው ችሎት ነው።

ትዕዛዙ የተላለፈው የግልግል ዳኞች ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም የሰጡትን ውሳኔ ለማስፈፀም ነው።

ችሎቱ ውሳኔው በሚፈለገው መንገድ እንዲፈፀም አዟል።

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ባቀረበው ሪፖርት፣ ቤቶቹ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 በይዞታ ቁጥር 10/69/1/6/43191/00 ላይ በሚገነባ አፓርትመንት ውስጥ እንደሚገኙ አረጋግጧል።

አፓርትመንቱ በኩባንያው ስም እንደተመዘገበ መረጋገጡንም በፍርድ ቤቱ ሰነድ ላይ ሰፍሯል።

በዚህ መሠረት ችሎቱ ፣ ግንባታቸው 80 በመቶና ከዚያ በላይ የደረሱ ቤቶች ዕዳውን ለመሸፈን በቂ ከሆኑ እነሱ ብቻ እንዲሸጡ አዟል።

በቂ ካልሆኑ ደግሞ ከዚያ በታች የግንባታ ደረጃ ላይ ያሉትም ዕዳውን ለመሸፈን በሚበቃ መጠን በጨረታ እንዲሸጡ ወስኗል።

ከሽያጩ ለባለመብቶች የተወሰነው ገንዘብ ከተቀነሰ በኋላ የሚቀረው ካለ ለኩባንያው እንዲመለስ ተብሏል።

ፍሊንትስቶንስ በሁለት አመት ከ6 ወር ቤቶችን አጠናቅቄ አስረክባለሁ ብሎ ከደንበኞቹ ጋር ውል ቢገባም በውሉ መሰረት ሰርቶ ቤቶቹን አለማስረከቡ ደንበኞቹ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት አንዲወስዱት አድርጓቸዋል፡፡

በዚህ መሰረት ከሳሾች በወቅቱ በነበረው የገበያ ዋጋ ማለትም በካሬ 99 ሺህ ብር ተሰልቶ ይሰጠን ሱሉም ለፍርድ ቤቱ አቤት ብለዋል።

የግልግል ዳኝነቱ በወቅቱ ኩባንያው ውሉን አለማክበሩን አረጋግጧል።

ነገር ግን ከሳሾች እንዲከፈላቸው ባመለከቱት ሳይሆን በካሬ 24 ሺህ ብር አስቦ እንዲሰጣቸው በፍሊንስቶንስ ኢንጅነሪንግ አ.ማ ላይ መፍረዱን ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ ተመልክተናል።

በውሳኔው ቅር የተሰኙት ከሳሾች ይግባኝ በማለት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቀርበው ጉዳዩን አስረድተዋል።

ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ የስር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ እንዳፀናው መዘገባችን ይታወሳል።

ከሶስት አመት በላይ በፈጀው ክርክር ህዳር 10/2019 ዓ/ም በዋለው ችሎት ቤቶቹ በሀራጅ ተሽጠው ለባለመብቶች እንዲከፈል ችሎቱ የአፈፃፀም ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ያልተፈፀመ ነገር ካለ መዝገቡ ለጊዜው ተዘግቶ ወደ መዝገብ ቤት እንዲመለስ ማለቱን ከፍርድ ቤቱ የትዕዛዝ ሰነድ ማየት ችለናል።

Via Sheger FM 102.1 RADIO

@etconp

Comments

Be the first to add a comment