👉የግንባታ ዋጋ ማስተካከያ (PRICE ADJUSTMENT)፤ ለሥራ ተቋራጮች የፕሮጀክት አፈጻጸም ዋስትና!
⏺በግንባታ ዘርፍ የሲሚንቶ፣ የብረት፣ የነዳጅ፣ የማጓጓዣና ሌሎች የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ መጨመር በፕሮጀክቶች ወጪ፣ የሥራ ሂደትና የማጠናቀቂያ ጊዜ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል።
▶️በተለይም በረጅም ጊዜ የሚከናወኑ የግንባታ ውሎች ውስጥ ከውሉ መጀመሪያ በኋላ የግብዓቶች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ሲለዋወጥ፣ የዋጋ ማስተካከያ (Price Adjustment) አስፈላጊ የውል አስተዳደር መሣሪያ ይሆናል።
🏛የዋጋ ማስተካከያ ለሥራ ተቋራጮች ምን ይፈይዳል?
🔹 በግብዓት ዋጋ ጭማሪ የሚመጣውን የወጪ ጫና ለመቀነስ ይረዳል።
🔹 በውል የተገባውን ሥራ በተቀመጠው ጥራትና ጊዜ ለማከናወን ያግዛል።
🔹 በዋጋ መለዋወጥ ምክንያት የሚፈጠርን የፋይናንስ ችግር ይቀንሳል።
🔹 በአሠሪና በሥራ ተቋራጭ መካከል የሚፈጠርን የውል ክርክር ለመከላከል ይረዳል።
🌟የሥራ ተቋራጮች ምን ማወቅ አለባቸው?
🔷በውላቸው ውስጥ የPrice Adjustment አንቀጽ መኖሩን ማረጋገጥ።
🔷 የዋጋ ለውጡን የሚያሳዩ ሰነዶችና ማስረጃዎችን ማዘጋጀት።
🔷 በውሉ የተቀመጠውን የስሌት ዘዴና የማመልከቻ ሂደት መከተል።
🔷 ማመልከቻዎችን በተወሰነው ጊዜና በተገቢው አካል ማቅረብ።
❓የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ በሚጨምርበት ወቅት፣ የዋጋ ማስተካከያ ሥርዓት በተገቢው ሁኔታ እየተተገበረ ነው ትላላችሁ ?
❓ለሥራ ተቋራጮች፣ ለአማካሪዎችና ለፕሮጀክት ባለቤቶች የእናንተ ልምድና አስተያየት ምንድን ነው?
👇 ሀሳባችሁን በኮሜንት ላይ እስኪ አጋሩን!
🌐ለተጨማሪ መረጃ እና ሌሎች የኮንስትራክሽን ዘርፍ ዜናዎች የ YouTube ገፃችን ከታች ባለው ሊንክ በመግባት SubScribe አርገው ቤተሰብ ይሁኑ
👇https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG
@etconp