🧱 በሊንቴል ቢም (Lintel Beam) እና በበሮች/መስኮቶች አናት ግንባታ ወቅት ሊደረጉ የሚገቡ ወሳኝ ጥንቃቄዎች!

​በምስሉ ላይ እንደሚታየው ከስር በቀይ ጡብ (Brick Plinth Work) ከተሰራ መሰረት በላይ የብሎኬት ግንብ (HCB Superstructure Wall) የተገነባ ሲሆን፤ በበሮች እና በመስኮቶች ክፍተት አናት ላይ የሊንቴል (Lintel Beam) ስራ ተከናውኗል።

​📌 በሳይት ደረጃ ለጥራት ቁጥጥር ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ነጥቦች፦

​1️⃣ የሊንቴል ቢም ጥቅም (Purpose of Lintel Beam): ከበሩ ወይም መስኮቱ በላይ የሚገነባው ግንብ ክብደት በቀጥታ በፍሬሙ (Door/Window Frame) ላይ አርፎ ጉዳት እንዳያደርስ ክብደቱን ወደ ጎን ግንቦች ያስተላልፋል።

2️⃣ የማረፊያ ርዝመት (Bearing Length): ሊንቴል ቢም ከክፍተቱ (Opening) አልፎ በሁለቱም ጎን ባሉት ግንቦች ላይ አነስተኛው ከ15 እስከ 20 ሴ.ሜ (cm) ማረፍ/መደገፍ አለበት።

3️⃣ ተከታታይ የሊንቴል ባንድ (Continuous Lintel Band): በተለይ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ባላቸው አካባቢዎች ሊንቴሉ በነጠላ ክፍተቶች ላይ ብቻ ሳይሆን በህንፃው ዙሪያ ሙሉ በሙሉ የታሰረ (Continuous Band) ሆኖ ቢሰራ የህንፃውን መዋቅራዊ ጥንካሬ በእጅጉ ይጨምራል።

4️⃣ የመሰረት እና የብሎኬት ስራ ትስስር: ከስር ያለው የቀይ ጡብ መሰረት እና የብሎኬት ግንቡ በትክክለኛ የሲሚንቶ ሞርታር ውህድ እና በሌቭል (Plumb/Level) መሰራቱን ማረጋገጥ።

​🌟አዳዲስ የስራ ቅጥሮች እና የኮንስትራክሽን ጨረታዎች ሲወጡ በቀላሉና በ ትኩሱ ለመመልከት ከታች ባለው ሊንካችን ይቀላቀሉን።

📌እንዲሁም ለወዳጆቻቹ SHARE ያርጉ👇

https://t.me/ETCONpWORK
https://t.me/ETCONpWORK

Comments

Be the first to add a comment