👉በዱባይ የሚገነባው አዲስ ሙዚየም በውሃ ላይ ይንሳፈፋል ተባለ

❇️የዱባይ ገዥ የሆኑት ክቡር ሼኽ መሐመድ ቢን ራሺድ አል ማክቱም በአል ፉተይም ግሩፕ የሚመራውን እና ለዱባይ አዲስ የስነ-ህንፃ እና የባህል ምልክት የሚሆነውን የዱባይ የስነ ጥበብ ሙዚየም  ንድፍ ይፋ አድርገዋል።

💫የዱባይ የስነ ጥበብ ሙዚየም የሚገነባው በዱባይ ክሪክ ውሃ ላይ ይሆናል።

💫ይህም ዱባይ የፈጠራ ኢኮኖሚ ዓለም አቀፍ ዋና ከተማ የመሆን ራዕይን እና የከተማዋን ቀጣይነት ያለው የባህልና የኪነጥበብ ልማት የሚያንጸባርቅ ይሆናል።

⏺አጠቃላይ የስነ ሕንፃው አሠራር ለጎብኚዎች ልዩ ልምድ በሚሰጥ መልኩ ተቀርጾል።

🚧አምስት ፎቅ ያለው ይህ የሚንሳፈፍ ሙዚየም በመጀመሪያው እና በሁለተኛው ፎቆች ላይ የኤግዚቢሽን ጋለሪዎች፣ በሦስተኛው ፎቅ ላይ ደግሞ ምግብ ቤት እና ለከፍተኛ እንግዶች  የሚሆን ላውንጅ ይኖረዋል።

⏺ሙዚየሙ የመሬት እና የመሬት ውስጥ (ቤዝመንት) ፎቆችም ይኖሩታል።

💫ከኪነ ጥበብ ሥራዎች ኤግዚቢሽን በተጨማሪም ሙዚየሙ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ውይይቶችን፣ የፓናል ውይይቶችን፣ የትምህርት ፕሮግራሞችን እና የስነ ጥበብ ትርኢቶችን ያዘጋጃል ተብሏል።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment