"ደረጃዉን ያልጠበቀ ግንባታ በማከናወን የተከሰሰዉ ግለሰብ በ5ዓመት ከ5 ወር እስራትና በገንዘብ ተቀጣ
❗️ተከሳሽ ይማም መሀመድ ተሰማ እድሜ 42 አድራሻ ደሴ ከተማ ቧነቧዉሃ /ክ/ከተማ የህንፃ አዋጅ ቁጥር 624/2001 አንቀጽ 53/2/ሀ/ እና /ለ/ ላይ የተመለከተዉን በመተላለፍ በወ/ሮ ሙሉ መሀመድ በተሰጠዉ የዉክልና ስልጣን መሰረት የህንፃ አዋጅ በሚፈቅደዉ አግባብ ለሚያከናዉነዉ ግንባታ ተገቢነት ያለዉ የህንፃ ግንባታ ባለሙያ አማካሪና ኮንትራክተር ይዞ ህንፃዉን ማስገንባት ሲገባዉ ለህንፃዉ ደረጃ በማይመጥንኑ ባለሙያ ባልሆኑ ሰዎች ጥር ወር 2017 ዓ.ም ህንፃ በማስገባቱ እና ከሚያከናዉነዉ ግንባታ ዉስጥ የህንፃዉ አካል የሆነዉን ሲፍቲ ታንከር ደረጃዉን ባልጠበቀ የግንባታ ቁሳቁስና ሊከተል የሚገባዉን የአገነባብ ሂደት ባለመጠበቅ ከደረጃ በታች የሆነ ግንባታ በመገንባቱ በፈጸመዉ ደረጃዉን ያልጠበቀ ግንባታ ማከናወን ወንጀል ክስ ተከሶ ምረመራዉን የደሴ ከተማ 4ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ አጣርቶ ለደሴ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት በማቅረብ ዐ/ህግም ክሱን በማጠናቀር ለደሴ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት አቀረበ፡፡
የደሴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ወንጀል ችሎት ጉዳዩን በመመርመር የሰዉና የሰነድ ማስረጃዎችን በማየትና በመስማት የጥፋተኝነት ዉሳኔ ሰጥቷል፡፡
በመሆኑም ችሎቱ ከከሳሽና ከተከሳሽ የቅጣት ማክበጃና መቅለያ አስተያየት በመቀበል ፍ/ቤቱ በቀን 3/04/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ጥፋተኛዉን ያርማል ሌሎችን ያስተምራል ባለዉ በ5 ዓመት ከ 5 ወር እስራት በገንዘብ መቀጮ ብር 8000/ስምንት ሽህ ብር/ እንድቀጣ ወስኗል።"
Via የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
@etconp