2.የሚስተባበል የሕሊና ግምት (rebuttable presumption)
-መነሻ የሚሆነዉ መሠረታዊ ፍሬ ነገር በማስረጃ መረጋገጥ ያለበት ሲሆን፤ አንድ ጊዜ ፍሬ ነገሩ ከተረጋገጠ ደግሞ በሌላ ተቃራኒ ማስረጃ እስካልተስተባበለ ድረስ ፍ/ቤቱ አከራካሪ የሆነዉ ፍሬ ነገርም እንደተረጋገጠ አድርጎ የሚገምትበትና የሚቀበልበት ነዉ፡፡
-ይህም ማስረጃ የማቅረብ ሸክምን ወደሌላኛዉ ወገን የሚያስተላልፍ ይሆናል
ለምሳሌ፡- የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1147(1)
ስለሌላ ሰዉ ሆኖ ባለይዞታ መሆንን የጀመረ ሰዉ ተቃራኒ የሆነ ማስረጃ ከሌለ በቀር ምንጊዜም በጠባቂነት እንደያዘ ሆኖ ይገመታል
-በዚህ መሠረት መሠረታዊ ፍሬ ነገር የሆነዉ ይዞታዉ በሌላ ሰዉ ስም መሆኑ በማስረጃ ከተረጋገጠ በቦታዉ ላይ ያለዉ ሰዉ ባለይዞታ ሳይሆን ጠባቂ ለመሆኑ መረጋገጡን ፍ/ቤት ግምት ይወስዳል፡፡
-ይህ የሚሆነዉ ግን ተቃራኒ ማስረጃ እስካልቀረበ ድረስ ብቻ ነዉ፡፡ በቦታዉ ላይ ያለዉ ሰዉ ጠባቂ አይደለሁም ሲል ለዚህ ተቃራኒ የሚሆን ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
ሕድአት ጌታቸዉ
የካቲት/2014 ዓ.ም

Comments

Be the first to add a comment