🔘ካርታ የሌላት መሬት▪️ወንድሜ ሆይ ዱኒያ የኮንትራት ምድር ናት፤ እሷ ላይ የመኖር ኮንትራታችን መቼ እንደሚያበቃ ማናችንም አናውቅም።
ዱኒያ ልክ ካርታ እንደሌለው መሬትም ናት፤ መች እንደምትፈርስ አይታወቅም።
የሷን መፍረስ ባታይም እድሜና ጉልበትህ ቀስ በቀስ እየፈረሰ አንተ ቀደመህ ትፈርሳለህ/ሽ።
▪️ስለዚህም በጤና፣ በወጣትነትና በከንቱ ምኞት ወዘተ. አንታለል!
▪️ሞት መችና በምን አቅጣጫ እንደሚመጣ አይታወቅም።
የመልካም ሥራ ሻንጣችንን ይዘን ሁሌም ዝግጁ ሆነን መጠበቅ ብቻና ብቻ ነው የሚያዋጣን።
ወደ ዋናው ሀገራችን (ኣኺራህ) ምን ይዘን እንደምንመለስ ዘወትር እናስብ።
▪️ትልቁ ድህነት ማለት የኣኺራህ ድህነት ነው።
ትልቁ ውርደትና መከራም የጀሀነም እስረኛ መሆን ነው።
▪️ትልቁ እድልና ስኬት ደግሞ በዱኑያ ቆይታ የተስተካከለ እምነት ላይ ሆኖ ብዙ መልካም ሥራዎችን ሰርቶ በመሄድ ኣኺራህ ላይ ጀነትን መሸለም ነው!
{ كُلُّ نَفۡسࣲ ذَاۤئقَةُ ٱلۡمَوۡتِۗ وَإِنَّمَا تُوَفَّوۡنَ أُجُورَكُمۡ یَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِۖ فَمَن زُحۡزِحَ عَنِ ٱلنَّارِ وَأُدۡخِلَ ٱلۡجَنَّةَ فَقَدۡ فَازَۗ وَمَا ٱلۡحَیَوٰةُ ٱلدُّنۡیَاۤ إِلَّا مَتَـٰعُ ٱلۡغُرُورِ }
[سُورَةُ آلِ عِمۡرَانَ: ١٨٥]
"ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፤ የስራችሁን ዋጋ የምታገኙት የቂያማ ቀን ነው።
ከእሳት ርቆ/ድኖ ጀነት የገባ ሰው በእርግጥም የምኞቱን በማግኘት ታድሏል።
ይህች የዱኒያ ህይወት መታለያ መገልገያ እንጂ ሌላ አይደለችም!" ኣል ዒምራን: 185
▪️አላህ የሁለት ዓለም ሕይወታቸውን ካሳመረላቸው ባሮቹ ያድርገን
🤲
✍ ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም 6/3/1448 ዓ.ሂ
🌱 @TewhedandSuna