👉ድምፃችን ተሰምቷል🙏

የታሪካዊውን ክቡ የንግድ ባንክ የፊት ገፅታን በእጅጉ የሚጎዳው ግንባታን ተከትሎ ያሰማነው ጩኸት ተሰምቶ በአሁኑ ሰዓት ግንባታው ሙሉ በሙሉ ተነስቷል።

ይህን መልዕክት እያስተላለፍኩ ያለሁት በአሁኑ ደቂቃ እዚያው ሕንፃው አጠገብ ሆኜ ነው።

የተቃውሞ ድምፃችንን ማሰማታችንን ተከትሎ ከጎናችን የቆማችሁትን፣ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ፣ ልጥፎችን ሪአክት በማድረግ፣ በኮመንትና ሼር በማድረግ የተባበራችሁትን በሙሉ ከልብ እናመሠግናለን።

የሕዝብን ቅሬታ ተከትሎ ለግንባታው መፍረስ ግንባር ቀደም ሚናውን የተጫወተው በኢ/ር ሕይወት ሳሙኤል ዋና ዳይርክተር የሚመራው የአዲስ አበባ ግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ስለመሆኑ መረጃው ደርሶናል፣ ከልብ እናመሠግናለን!

እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ከግንባታ ፈቃድ ቁጥጥር ባለሥልጣን ጋር በመሆን ድምፃችን በመስማቱ ምሥጋናችን የላቀ ነው!።

ምንጭ ጌታሁን ሔራሞ

@etconp

Comments

Be the first to add a comment