የቢሾፍቱ ግዙፍ የአውሮፕላን ማረፊያ የግንባታ ምዕራፍ ተጀመረ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ የሚገነባውን አዲሱንና ግዙፉን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ዲዛይን እና የግንባታ ክትትል ሥራ ለታዋቂው የሕንፃ ጥበብ ድርጅት ዛሃ ሃዲድ አርኪቴክቸር መስጠቱን ተከትሎ የግንባታው ሂደት በይፋ መጀመሩን ወርልድ አርክቴክቸር ዘግቧል።
ይህ 6 ቢሊዮን ዶላር የሚፈጅ ሜጋ ፕሮጀክት በዋናነት በብድር በሚገኝ ፋይናንስ የሚከናወን ሲሆን፣ ሲጠናቀቅም በዓመት 100 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል ተብሏል።
አየር መንገዱ አሁን ካለበት የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የማስተናገድ አቅም በላይ እያደገ በመምጣቱ፣ ይህ አዲስ ፕሮጀክት ለአፍሪካ አቪዬሽን ኢንዱስትሪ ትልቅ ስትራቴጂካዊ መፍትሔ ሆኖ ቀርቧል።
@etconp