⚠️ የኮንስትራክሽን ኪሳራ ከየት ይጀምራል? ከአሰሪው “ቅበላ” ወይንስ ከኮንትራክተሩ ጥራት?
በኢንጅነር ደሳለኝ ከበደ ፅሁፍ የጀመርነው ትንተና ሌላ ዋና ባለድርሻ እንድናስብ አደረገን።
አሰሪው (Client) ዝም ብሎ ተመልካች መሆን የለበትም፤ ኃላፊነት አለበት። በተለይ መቶ ሚሊዮን የተገመተን ፕሮጀክት በሰባ ሚሊዮን “ሲቀበል” (Underbidding ሲደረግ) ኪሳራው ገና ሳይት ሳይገባ በወረቀት ላይ ተፈርሟል ማለት ነው።
ባለፈው በአማካሪዎች ድክመት ዙሪያ ያነሳነው ነጥብ እንዳለ ሆኖ፣ ሌላውና ትልቁ የዘርፉ በሽታ የሚጀምረው ከራሱ ከአሰሪው (Client) ነው። አሰሪው “ፕሮጀክቴ የት ላይ ነው? ምን እየተሰራ ነው?” ብሎ የመከታተል ብቻ ሳይሆን፣ ገና በጨረታው ወቅት የሚሰራው ስህተት ለፕሮጀክቱ መክሸፍ ትልቅ ምክንያት ነው።
ለምሳሌ ያህል፦
💰 በአግባቡ ተጠንቶ 100 ሚሊዮን ብር ይፈጃል የተባለውን ግንባታ፣ አሰሪው ወጪ ለመቀነስ ብቻ በማሰብ ወይም በጥናት ላይ ባልተመሰረተ ፉክክር በ70 ሚሊዮን ብር ተደራድሮ “ሲቀበለው” ችግሩ ከዚያው ይጀምራል!
ይህ በምህንድስናው ዓለም "Underbidding" (ካለ አግባብ ዋጋን መስበር) የሚባለው አካሄድ የሚያስከትላቸው አስከፊ መዘዞች፦
1.
📉 ጥራትን መበለዝ፦ ኮንትራክተሩ ከኪሳራ ለመዳን ሲል ማቴሪያልና የሙያ ጥራትን ለመቀነስ ይገደዳል።
2.
⏳ የተጓተቱ ፕሮጀክቶች፦ በሂደት ላይ የገንዘብ እጥረት (Cash Flow) ስለሚገጥም ስራው ይቆማል፤ በመጨረሻም አሰሪው ካሰበው በላይ ለወጪና የጊዜ ብክነት ይጋለጣል ።
3.
🤝 የ "Plan vs. Site" አለመጣጣም፦ ጥራቱ ያልተጠበቀ ጨረታ በመጨረሻም በወረቀት ላይ ያለው ፕላን እና ሳይት ላይ የሚሰራው ጉድኝት እንዳይገጥም ያደርገዋል::
የናሽናል ኮንስትራክሽን ሚዲያ መልዕክት፦
አሰሪው ዝቅተኛ ዋጋ ስላገኘ ብቻ ያሸነፈ መስሎት ከሆነ ተሳስቷል! ጥራት ያለው ግንባታ የሚገኘው ተገቢው ዋጋ ለተገቢው ባለሙያና ማቴሪያል ሲሰጥ ብቻ ነው። አሰሪዎች ዋጋ ከመቁረጥ ባለፈ “ፕሮጀክቴ የት ላይ ነው?” ብለው ጥራቱን የመቆጣጠር ትልቅ የቤት ስራ አለባቸው።
📱 ባለሙያዎች ምን ትላላችሁ?
ይህ 100 ሚሊዮን የተገመተን ስራ በ70 ሚሊዮን ብር የመቀበል ልምድ በሃገራችን ኮንስትራክሽን ላይ ምን ያህል ጉዳት እያደረሰ ነው? መፍትሔውስ ምንድነው?
ሃሳባችሁን በኮሜንት አጋሩን!
👇@etconp