የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
ጤና ይስጥልኝ፡-
ለዜጎች ከሚቀርቡ ፍጆታዎች አንዱ የኤሌክትሪክ ኃይል ሲሆን ይህንነን ኃይል መስረቅ በእሥራት ወይም እስከ ብር ሃያ ሺህ በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ወይም በሁለቱም እንደሚቀጣ ስለዚሁ ከወጣው የኢነርጂ አዋጅ ቁጥር 810/2006 የተቀመጠውን ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ አቅርበነዋል፡፡ መልካም ንባብ
የኢነርጂ አዋጅ ቁጥር 810/2006
አንቀጽ 28፡- የኤሌክትሪክ ኃይል ስለመስረቅ
ማናቸውንም የኤሌክትሪክ ኃይል የሰረቀ፣ በሕገ-ወጥ መንገድ ከሌላ መስመር ጋር ያገናኘ፣ መስመሩን ያሰናከለ ወይም የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲሰርቅ፣ ከሌላ መስመር ጋር እንዲገናኝ ወይም መስመሩ እንዲሰናከል ያደረገ ወይም መስመሩ የተሰረቀ፣ በሕገ-ወጥ መንገድ ከሌላ መስመር ጋር የተገናኘ ወይም የተሰናከለ መሆኑን እያወቀ ከዚሁ መስመር ማናቸውንም የኤሌክትሪክ ኃይል ለፍጆታ ያዋለ ወይም የተገለገለ እንደሆነ እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ወይም እስከ ብር 20‚000 (ሃያ ሺህ ብር) በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ወይም በሁለቱም እንደሚቀጣ ተደንግጓል፡፡
ደረጀ ማርቆስ
ታህሳስ 2013 ዓ.ም
Comments
Be the first to add a comment