🏗️የዚህ ፉቲንግ ስም ማን ይባላል?
🤔በምስሉ ላይ በቀይ ቀስት የተመለከተው ፉቲንግ ወደ ላይ እየጠበበ የሚሄድ ተዳፋት ቅርጽ አለው።
በኢንጂነሪንግ Sloped Footing ወይም Trapezoidal Footing ይባላል።
📌 እንግዲህ ይህ ፉቲንግ ለምን እንዲህ ተዳፋት ሆኖ ይሰራል?
🔹 የኮንክሪት ብክነትን ለመቀነስ – ከኮለሙ አካባቢ ወፍራም ሆኖ ወደ ጫፉ እየቀነሰ ስለሚሄድ አስፈላጊ በሆነው ቦታ ብቻ ኮንክሪት ለመጠቀም ያግዛል።
🔹 ጭነትን ወደ መሬት ለማስተላለፍ – ከኮለሙ የሚመጣውን ጭነት ተቀብሎ በፉቲንጉ በኩል ወደ አፈር ያስተላልፋል።
🔹 ቁሳቁስን በተመጣጣኝ ለመጠቀም – በትክክለኛ ዲዛይን ሲደረግ ከቀጥተኛ የሆነ Isolated Footing ጋር ሲነጻጸር የኮንክሪት መጠንን ሊቀንስ ይችላል።
⚠️ በሳይት ላይ ግን እነዚህን ነጥቦች አትዘንጉ!
1️⃣ Concrete Slump – ኮንክሪቱ በጣም ፈሳሽ ከሆነ ተዳፋቱን ቅርጽ ሊያጣ ይችላል።
2️⃣ Compaction – ኮንክሪቱ በደንብ ካልተጠቀጠቀ የHoneycombing ችግር ሊፈጠር ይችላል።
3️⃣ PCC & Concrete Cover – ከፉቲንጉ ስር የሚደረገው PCC (Lean Concrete) በትክክል መዘርጋቱን እና የConcrete Cover መጠኑ በዲዛይኑ መሰረት መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል።
💬 እስኪ እናንተ ምን ትሉታላችሁ?
Sloped Footing ወይስ Trapezoidal Footing?
👇
💡 ተመሳሳይ የሳይት ኢንጂነሪንግ መረጃዎችን ለማግኘት የፌስቡክ ገፃችን Follow ያድርጉ
👇https://www.facebook.com/profile.php?id=61592085774934@etconp