ከዛሬ ከነሐሴ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ፍርድ ቤቶቹ በከፊል ዝግ ሆነው ሁለት ወራት ጊዜ ይቆያሉ ነገር ግን በባህሪያቸዉ አስቸኳይ የሆኑና ጊዜ የማይሰጡ እንዲሁም ለዉሳኔ የደረሱ መዛግብትን መርምሮ ውሣኔ የመስጠት አገልግሎቶች እንደሚቀጥሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አሳውቋል።

በክረምቱ ወቅት አገልግሎታቸው የሚቀጥሉ መዝገቦች የትኞቹ ናቸው ?

- ህጻናት ለያዙ ሴቶችና በህፃናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን የሚመለከት ጉዳዮች፣

- ወጣት ጥፋተኞችን የሚመለከት የይግባኝ ጉዳዮች

- ለወንጀል ምርመራ በቀረበ የጊዜ ቀጠሮና ዋስትናን በሚመለከት በተሰጠ ትዕዛዝ ወይም በውሣኔ ላይ የቀረበ ወይም የሚቀርቡ የይግባኝ ክርክሮች ወይም አቤቱታዎች፣

- የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ወንጀል ሕግ አንቀፅ 201 እና በተከታዮቹ በተደነገገው መሰረት የሚቀርብ በአመክሮ መለቀቅን እንዲሁም በአንቀፅ 175 በተደነገገው መሰየምን በሚመለከት የሚቀርቡ አቤቱታዎችንና ክርክሮችን፣

- እግድንና እና መፈቻን በሚመለከት የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እንዲሁም ሌሎች አስቸኳይነታቸዉ በችሎቱ የሚለዩ መሰል ጉዳዮችን፣

- በፍትሐብሔር ጉዳዮች የቀለብና ተያያዥነት ያላቸዉ የቤተሰብ ጉዳዮች ላይ የሚቀርብ አቤቱታና ክርክር፣ የእግድና እንደ አስፈላጊነቱ አስቸኳይ መፍትሔ የሚፈልጉ አቤቱታዎች ይታያሉ።

በእዚህም መሰረት:-

° የሰበር አጣሪ ችሎቶች በመደበኛ ጊዜ የሚሰራዉን አጣርቶ ዉሳኔ የመስጠት ስራን ከነሐሴ 1ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ በመደበኛ የዳኝነት አገልግሎት መስጠት ይቀጥላሉ።

° ፌደራል ጠቀላይ በተረኛ ችሎት የሚሸፈነው ጊዜ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ከጳጉሜ 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ ሲሆን በፌዴራል ከፍተኛ እና መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከነሃሴ 01 ቀን 2017 ጀምሮ እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ ይሆናል።

Comments

Be the first to add a comment