👉ተደርቦ በተሰራ ካርታ እና በይዞታ መብት ላይ የተሰጠ የሰበር ውሳኔ!

🏛ድርብ ካርታ ሲኖር ቀድሞ ያስመዘገበው ሰው ቦታው ይገባዋል፤ ዘግይቶ ካርታ ወስዶ የገነባው ሰው ደግሞ ቤቱን አፍርሶ ቦታውን የመልቀቅ ግዴታ አለበት ሆኖም ላጋጠመው ኪሳራ ስህተት የፈጸመውን የመንግስት አካል ከሶ ካሳ ማግኘት ይችላል። ሰ.መ.ቁ 246230

​ይህ የሰበር ውሳኔ በአንድ የከተማ መሬት ላይ ለሁለት የተለያዩ ሰዎች ደርቦ (ድርብ) ካርታ በሚሰጥበት ጊዜ የሚነሳን የባለቤትነት ክርክር የሚያስረግጥ ሲሆን፣ ዋና ዋና ነጥቦቹ የሚከተሉት ናቸው፦

​1. የቀዳሚነት መብት (የመጀመሪያው ካርታ የበላይነት)

​በአንድ ይዞታ ላይ ለሁለት ሰዎች ካርታ ከተሰጠ እና ዘግይቶ ካርታ ያወጣው ሰው በቦታው ላይ ቤት ቢገነባበት እንኳ፣ ትክክለኛና ሕጋዊ መብት ያለው ቀድሞ ካርታ የወሰደው (ያስመዘገበው) ሰው ነው።

በመሆኑም ዘግይቶ የመጣው አካል የሰራውን ቤት አፍርሶ ቦታውን ለቀዳሚው ባለካርታ ማስረከብ አለበት።

​2. የሕግ መሠረት (አዋጅ ቁጥር 818/2006)

​በሀገሪቱ ባሉ ከተሞች ሁሉ ተፈጻሚነት ባለው የፌደራል "የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 818/2006 አንቀጽ 43" መሠረት፦

​ሁለት ሰዎች በአንድ መሬት ላይ ተመሳሳይ መብት ቢጠይቁ፣ ቅድሚያ የሚሰጠው በመሬት ይዞታ መብት መዝገብ ውስጥ ቀድሞ መብቱን ላስመዘገበው ሰው ነው።

​ስለዚህ የይዞታ ባለቤትነት የሚወሰነው በምዝገባ ቅደም-ተከተል ወይም ቀድሞ በተገኘ መብት ላይ ብቻ ነው።

​3. የካሳ መብት (ፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1198)

​ሕጋዊ ባልሆነ (በተደራቢ) የይዞታ ማረጋገጫ ምክንያት ቤቱን እንዲያፈርስና ቦታውን እንዲለቅ የተፈረደበት ሰው የመካስ መብት አለው፦

​ይህ አካል በሕግ አግባብ ባልተሰጠው የካርታ ማረጋገጫ ምክንያት ለደረሰበት ጉዳት እና ኪሳራ የመንግስትን አካል (የመሬት አስተዳደሩን) ከሶ ካሳ የመጠየቅና የማግኘት ሙሉ ሕጋዊ መብት አለው።

​​🌐ለተጨማሪ መረጃ እና ሌሎች የኮንስትራክሽን ዘርፍ ዜናዎች የ YouTube ገፃችን ከታች ባለው ሊንክ በመግባት SubScribe አርገው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG
‎
‎@etconp

Comments

Be the first to add a comment