የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
ሰላም ጤና ይስጥልኝ እንዴት ሰነበታችሁ የምንገኝበት ወር ከሴቶች መብት መከበርን በተመለከተ የምናነሳበት ማርች ወር እንደመሆኑ መጠን በሕጎቻችን ሴቶችን በተመለከተ የተካተቱ መብቶችን እናጋራለን መልካም ንባብ
በሃገራችን ሴቶች ሲደርስባቸዉ ከነበረዉ ዘርፈ ብዙ ማሕበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጫና አንጻር ለመብት ጥሰጥ ተጋላጭ ተደርገዉ ከተለዩ የማህበረሰብ ክፍሎች አንዱ በመሆናቸዉ እና ይህንንም ለማስቀረት የሴቶች መብትን በሚመለከት ልዩ የሕግ ጥበቃ የሚያስፈልገዉ በመሆኑ በኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 35 የሴቶችን መብት ከተቃራኒ ጾታ መብት እኩልነት አንጻር፤ በጋብቻ፤ በባሕል በማህበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ሊኖራቸዉ/ሊጠበቅላቸዉ የሚገባ መብት እና ሌሎችንም በማካተት ተደንግጓል፡፡
የኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 35
ሴቶች ይህ ሕገ መንግሥት በአረጋገጣቸው መብቶችና ጥበቃዎች በመጠቀም ረገድ ከወንዶች ጋር እኩል መብት አላቸው፡፡
• ሴቶች በዚህ ሕገ መንግሥት በተደነገገው መሰረት በጋብቻ ከወንዶች ጋር እኩል መብት አላቸው፡፡
• ሴቶች በበታችነትና በልዩነት በመታየታቸው የደረሰባቸውን የታሪክ ቅርስ ከግምት ውስጥ በማስገባት ይህ ቅርስ እንዲታረምላቸው በተጨማሪ የድጋፍ እርምጃዎች ተጠቃሚ የመሆን መብት አላቸው፡፡ በዚህ በኩል የሚወሰዱት እርምጃዎች ዓላማ በፖለቲካዊ፣ በማኅበራዊና በኢኮኖሚያዊ መስኮች እንዲሁም በመንግሥት እና በግል ተቋሞች ውስጥ ሴቶች ከወንዶች ጋር በእኩልነት ተወዳዳሪና ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ እንዲቻል ልዩ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡
• ሴቶች ከጐጂ ባሕል ተጽዕኖ የመላቀቅ መብታቸውን መንግሥት ማስከበር አለበት፡፡ ሴቶችን የሚጨቁኑ ወይም በአካላቸው ወይም በአዕምሮአቸው ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ሕጐች፣ ወጐችና ልማዶች የተከለከሉ ናቸው፡፡
ሕድአት ጌታቸዉ
መጋቢት/2014 ዓ.ም
Comments
Be the first to add a comment