👉Drawing እና Specification ሲጋጩ፣ ማን ያሸንፋል?

Based on Fidic Redbook

የግንባታ ሳይት ላይ ደጋግሞ የሚያጋጥም ነገር አለ። ለምሳሌ ኮንትራክተር ኮለሙን (column) Drawing ላይ በተቀመጠው መሠረት በትክክል ይገነባል፤ Inspection ላይ ግን Resident Engineer መጥቶ Specification ውስጥ የተለየ concrete cover ተጠቅሶ እንዳገኘ ይነግርሃል፣ ሥራውንም ውድቅ ያደርገዋል።

የኮንትራት ሰነዶች ቅደም ተከተል ካላወቅህ፣ የምታጠፋው rework ብቻ ሳይሆን ማንን ተጠያቂ ማድረግ እንዳለብህ እንኳ ግራ ይገባሃል።

እዚህ ጋር ግን ቀድሞ ማወቅ ያለብህ ነገር አለ፦ ሰነዶቹ ከመጋጨታቸው በፊት አብረው መነበብ አለባቸው። General Conditions ራሱ ሁሉም ሰነዶች mutually explanatory እንደሆኑ ይደነግጋል፤ አንዱን ወደጎን ትተህ ሌላውን ብቻ መከተል አትችልም። Drawing ብዙ ጊዜ ጂኦሜትሪና location ሲያሳይ፣ Specification ደግሞ ስለ material, tolerance እና testing ይናገራል፤ በትክክል የማይጋጩ ከሆነ ሁለቱንም ማክበር አለብህ እንጂ የፈለከውን መምረጥ አይደለም ጉዳዩ።

እውነተኛ conflict ሲፈጠር ብቻ ነው Sub-Clause 1.5 ወደ ሥራ የሚገባው። ይህ ንዑስ አንቀጽ የሰነዶችን ደረጃ በዚህ ቅደም ተከተል ያስቀምጠዋል

a. Contract Agreement
b. Letter of Acceptance
c. Letter of Tender
d. Particular Conditions Part A – Contract Data
e. Particular Conditions Part B – Special Provisions
f. General Conditions
g. Specification
h. Drawings
i. Schedules
j. JV Undertaking (ኮንትራክተሩ JV ከሆነ)
k. ሌሎች የኮንትራት ሰነዶች

Specification ደረጃ (g) ላይ ተቀምጦ Drawings ከሱ በታች (h) ላይ ስለሚገኝ፣ ቀጥታ ግጭት ካለ Specification ያሸንፋል። ስለዚህ በምሳሌያችን ላይ RE ውድቅ ማድረጉ ትክክለኛ ውሳኔ ነው።

ደረጃውን ማወቅ ብቻ ግን በቂ አይደለም። ከፍ ያለ ደረጃ ያለውን ሰነድ እናውቃለን ብለክ ራስክ ወስነክ መስራት የለብክም። Sub-Clause 1.5 የሚጠይቀው ግልጽ ነው፦ አሻሚነት ወይም ልዩነት እንዳገኘክ ወዲያውኑ ለ Engineer Notice ላክ፣ ችግሩን በዝርዝር ግለጸው። RE ደግሞ ካንተ Notice ደርሶት ወይም ራሱ አይቶት፣ ማብራሪያ ወይም መመሪያ የመስጠት ግዴታ አለበት።

በአጭሩ፦ ቀጥታ ግጭት/ discrepancy ካለ Specification ከ Drawings በላይ ነው። ግን ልምድ ያለው ባለሙያ የሚሠራው በግምት አይደለም፤ ሥራውን አቁሞ፣ መደበኛ Notice አቅርቦ፣ በተለይ እንደ concrete ሙሌት ያለ irreversible ስራ ከመጀመሩ በፊት የ RE የጽሑፍ ውሳኔ ይጠብቃል።

እስኪ ይሄ ነገር site ላይ ብዙ ጊዜ የገጠመው እንዴት ፈታቺሁት comment ላይ አጋሩን

👉የኮንስትራክሽን ሥራ ውል አዘገጃጀት — ሙያዊ መመሪያ በአማርኛ

🏛የኮንስትራክሽን ሥራ ውል ከመዘጋጀቱ በፊት ሊታወቁና ሊካተቱ የሚገባቸውን ዋና ዋና ጉዳዮች በአማርኛ የሚያብራራ ሙያዊ መመሪያ።

ውል በኮንስትራክሽን ሥራ ውስጥ የባለቤትና የተቋራጭ መብትና ግዴታን በግልጽ ለማስቀመጥ፣ አለመግባባቶችን ለመቀነስ እና የሥራ ሂደቱን በተደራጀ መልኩ ለመመራት አስፈላጊ ነው።

👷 ሲቪልና ኮንስትራክሽን መሐንዲሶች
⚖️ የሕግ ባለሙያዎች
🏗️ ተቋራጮችና አማካሪዎች
📋 ፕሮጀክት ማኔጀሮች
🎓 የኮንስትራክሽን ተማሪዎች የሚጠቅም ምርጥ መፅሐፍ ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a9aa58c0b37b_etconp

Comments

Be the first to add a comment