ጤና ይስጥልኝ
ጤናማ አካባቢ መፍጠርንም ሆነ ሁኔታዎች የማመቻቸት መንግሥት ግዴታ ያለበት እንደመሆኑና ይህንኑም ለመወጣት ማስፈጸሚያ ድንጋጌ መኖር ያለበት በመሆኑ “የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112/2011‘’ ወጥቶ በሥራ ላይ የዋለ ሲሆን ለዛሬው ከዚሁ አዋጅ ላይ ለግንዛቤ ያህል እናስፍር ፡፡
መልካም ምንባብ፡-
በአዋጁ አንቀጽ 48 እና ተከታታይ አናቅጽቱ እንደምንረዳዉ ማንኛውም ሰው ለሕዝብ ክፍት በሆነ ማንኛውም ቦታ ከበር መልስ ባለ ማንኛውም የሥራ ቦታ በሁሉም የሕዝብ መጓጓዣ እና በጋራ መኖሪያ ቤት በማንኛውም የጋራ መገልገያ ቦታ ላይ ማጨስ ወይም ትምባሆን መጠቀም የተከለከለ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል ::
ፈጠሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ !!!
ደረጀ ማርቆስ
የካቲት 2014 ዓ.ም

Comments

Be the first to add a comment