🌙በለይለቱል ቀድር ሌሊት ምን መደረግ አለበት❕⏰️ በዚህ ታላቅ ሌሊት ሊከናወኑ የሚገቡ አራት ዋና ዋና ተግባራት፦
•
መስገድ (ቂያሙለይል)፦ "ለይለቱል ቀድርን አምኖና ከአላህ ምንዳን ፈልጎ የሰገደ ሰው ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል።"
•
በመስጂድ መቆየት (ኢዕቲካፍ)፦ በዚህች ሌሊት በመስጂዶች ውስጥ ተገልሎ አምልኮን ማብዛት የተወደደ ተግባር ነው።
•
ዱዓ ማድረግ፦ አይሻ (ረ.ዐ) "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ለይለቱል ቀድር ካገኘው ምን ልበል?" ብለው ሲጠይቁ፤ እሳቸውም፦ "አላሁመ ኢነከ ዓፉዉን ቱሒቡል ዓፍወ ፈዕፉ ዓኒ" (ጌታዬ ሆይ! አንተ ይቅር ባይ ነህ፣ ይቅርታንም ትወዳለህና ይቅር በለኝ) በይ አሏቸው።
•
ቁርዓን መቅራት፦ በተለይ በዚህች ሌሊት ቁርዓንን በብዛት መቅራት እጅግ አስፈላጊ ነው።
እነዚህን አራት ተግባራት በመፈጸም ቢዚ መሆን ፤ ከሌሎች ስራዎች ሁሉ በላጭና የተመረጡ ናቸውና።🔵 @TewhedandSuna 🌐