ከ20 ሺህ በላይ ይዞታዎችን ለማረጋገጥ ዝግጅት ተደርጓል

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የይዞታ ማረጋገጥና ምዝገባ ሥራዎችን ለማከናወን በየካ ክፍለ ከተማ የቅድመ ይዞታ ማረጋገጥ ዝግጅት ሥራዎች ያሉበት ደረጃ በይዞታ ማረጋገጥ አረጋጋጭ ሹሞች ተሳትፎ ተገምግሟል፡፡

በግምገማ መድረኩ በክፍለ ከተማው በሚገኙ ስድስት ወረዳዎችና 20 ቀጠናዎች ከ20 ሺህ በላይ ቁራሽ መሬቶችን በማረጋገጥና በመመዝገብ ለማስተናገድ የታቀደ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በመድረኩ የተሳተፉት አረጋጋጭ ሹሞች ወደ ሙሉ የይዞታ ማረጋገጥ ትግበራ ለመግባት የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እያከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በውይይቱ የተገኙት የይዞታ ማረጋገጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ባህሩ ግርማ በቅድመ ይዞታ ማረጋገጥ ሥራዎች ወቅት የታዩ ክፍተቶችን በማረም የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በተቀናጀ ሁኔታ ማጠናቀቅ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

@etconp

Comments

Be the first to add a comment