👉የሥራ ተቋራጭ (Contractor) የሕግ ተጠያቂነት

🚧በኮንስትራክሽን ውል ሁለት አይነት የግንባታ ሾል ርክክቦች ያሉ ሲሆን እነሱም  ግዚያዊ ርክክብ እና የመጨረሻ ርክክብ በመባል ይታወቃሉ፡፡

🏷1/ ግዚያዊ ርክክብ

⏺ግዜአዊ ርክክብ በተለይ በኮንስትራክሽን ውል የተመለከቱ የግንባታ ስራዎች ተከናውነው ካበቁ በኋላ ወዲያውኑ ሁለቱ ወገኖች ማለትም አሰሪውና ተቋራጩ ባሉበት በስራው ላይ የሚደረግ የምርመራ ማረጋገጫ ነው:: (የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3274(1)):: ይሄውም አሰሪው በትክክል የተገነባውን ግንባታ በእጁ አግብቶ መያዙን ጭምር ያረጋግጣል፡፡
⏺ስለዚህ ጊዜአዊ ርክክብ በዋናነት የተሰራውን የግንባታ ሾል አሰሪው መብቱን ጠብቆ በመጀመሪያ የሚረከብበት ሂደት ነው፡፡  በስራው ላይ ምርመራ መደረጉንም የሚያረጋግጥ ነው፡፡

⏺እንግዲህ ስራው ከተመረመረ በኋላ አሰሪው ያላመነበትን ግንባታ ፈርሶ እንደገና እንዲሰራ ወይም እንዲጠገን ተደርጐ የጥራት ደረጃውን ባሟላ ሁኔታ እንዲከናወን ለማዘዝ እንደሚችል ፒፒኤ ክሎስ 85 ይፈቅድለታል:: በዚህም መሰረት ግንባታው የስራ ምርመራውን ካለፈ አሰሪው ግንባታውን የሚረከበው ይሆናል፡፡

🏷2/ የመጨረሻ ርክክብ
የመጨረሻ ርክክብ/Final Acceptance/

⏺በተለይ የድህንነት ጊዜ ካለቀ በኋላ እና ተቋራጩ ጠቅላላ ግዴታዎቹን በደህና ሁኔታ የፈጸመ መሆኑን አሰሪው ሲያረጋግጥ ግንባታውን ሙሉ በሙሉ በእጁ የሚያደርግበት ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3279 ይደነግጋል፡፡

⏺የመጨረሻ ርክክብ አሰሪውና ተቋራጩ ባሉበት በጽሁፍ መደረግ እንዳለበት በአስገዳጅ ሁኔታ በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3279(2) ላይ ተደንግጓል፡፡ 

⏺በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3282 ላይ እንደተቀመጠው ከመጨረሻ ርክክብ በኋላ ተቋራጩ እስከ 10 አመት ድረስ ስለስራው አሰራር ጉድለት ተቋራጩ ሀላፊነት አለበት ፣ ለስራው ጥራት መድህን ሆኖም ይቀጥላል፡፡ ስለሆነም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተደረመሰውን ድልድይ የገነባው ሥራ ተቋራጭ ለደረሰው ጉዳት በሕግ ተጠያቂ የሚሆንበት አግባብ ሊኖር ይችላል:: ይሁን እንጂ በመጨረሻ ርክክብ ወቅት የሚታዩ ለነበሩ የጥራት ጉድለቶች ተቋራጩ ሀላፊነት የለበትም፡፡

@etconp

Comments

Be the first to add a comment