👉ተገጣጣሚ ቤቶችን በሶስት ወር  መገጣጠም  የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።

🚧ሊንክ አስ እና ጢግሮስ ትሬዲንግ አዲስ ነገር ይዘው መጥተዋል። ከዚህ ቀደም የኤሌክትሪክ መኪና ከቻይና በማስመጣት እና ብርሃን ገበያ በሚል ስያሜ በሽዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርገ የሱቅ ፕሮጀክቶችን ይፋ በማድረግ  ወደ ተግባር የገቡት እነዚህ ተቋማት አሁን ላይ ከቻይናው ሻንዶንግ ሊማኦቶንግ ከተባለ ድርጅት ጋር በቀጣይ በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመዋል።

⏺ሊንከ አስ እና ጢግሮስ ትሬዲንግ ከሻንዶንግ ሊማኦቶንግ  ድርጅት በቀጣይ  በሃገር ውስጥ ገበያ ከፍተኛ ፍላጎት እያሳየ ያለውን የኤሌክትሪክ መኪና ማስመጣት እንዲሁም  ከውጭ  ከማስገባት ባሻገር በሃገር ውስጥ የመገጣጠም እና የኤሌክትሪክ ቻርጅ ጣቢያዎች ግንባታ  እንዲሁም  በዝቅተኛ ዋጋ ተገጣጠሚ ቤቶችን መገንባት – ከኢትዮጵያ የግብርና ምርቶች መካከል ቡና ማር እና አቮካዶን ለቻይና ገበያ ማቅረብ  እንዲሁም  ጥራታቸውን  የጠበቁ  የተለያዩ የቻይና ምርቶችን ወደ ሀገር  በማስገባት እና  እንዲሁም ዓለም ዓቀፍ ኤግዚብሽንና ባዛርን በጋራ ለማዘጋጀት የሚያችል ስምምነትን ፈፅመዋል  ፡፡

⏺ይህ ስምምነት ዕቃዎችን ወይንም ምርቶችን ከሃገር ወደ ሃገር የማድረስ ጉዳይ ሳይሆን በምርት ሂደትና ተሳትፎ በስራ ዕድል ፈጠራ  ላይ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ጉልህ ድርሻ አለው ያሉት የሊንክ  አስ ትሬዲንግ ዋና ሾል አስፈፃሚ አቶ ፊልሞን ካሳሁን ሲሆኑ በተመሳሳይ የጢግሮስ ትሬዲንግ ዋና ሾል አስፈፃሚ አቶ ብርሃኔ  ጌታቸው በተለይ ተገጣጣሚ ቤቶቹ  የህብረተሰቡን የቤት ችግር በመቅረፍ  የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ ነው ይህንንም በአጭር ጊዜ ወደ ተግባር እንቀይራለን ነው ያሉት ፡፡

🏷የሻንዶንግ ሊማኦቶንግ  ድርጅት ዋና ሾል አስፈፃሚ  ሚስ ሆው ሚን ኢትዮጵያ የቀደምት የሰው ልጆች መገኛ መሆኗን ገልፀው ድርጅታቸው ይህንን የጋራ ሾል ለመስራት ዕድል በማግኘቱም ደስተኛ መሆናቸውን የገለፁት  ሃላፊዋ እንደ ሃገር በተለይ ለታዳሽ ሃይል የተሰጠው ትኩረት ሰፊ መሆኑን እና ይህንንም   ለመደገፍ የሚያስችሉ  ስራዎች በቴክኖሊጂ ሽግግር ተጠቃሚ ለማድረግ   ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀው በዚህ ስምምነት መሰረትም ጥራት ያለው ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ይሰራል ስለሆነም ከሊንክ አስ እና ጢግሮስ ትሬዲንግ ላይ የተደረገው የጋራ ስምምነት  ወደ ሙሉ ትግበራ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

💫ሊንክ አስ እና ጢግሮስ ትሬዲንግ ብርሃን ገበያ የተሰኘ ወጣቶችን የሱቅ ባለቤት የሚያደርግ ፕሮጀክት ከወራት በፊት ይፋ ያደረጉ ሲሆን የዚህ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር የሱቅ ርክከብም የፊታችን አርብ ነሃሴ 02/2017 ዓ.ም በአምቦ ከተማ ርክክብ  የሚያደርግ ይሆናል፡፡

መረጃው ከሊንክ አስ ከጢግሮስ ትሬዲንግ  እና የሻንዶንግ ሊማኦቶንግ  ድርጅት የተገኘ
ነው።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment