ሰላም ጤና ይስጥልኝ በዚህ ጽሁፍ ስለ ሕሊና ግምት ይዘን ቀርበናል መልካም ንባብ……
የሕሊና ግምት አይነቶች (types of presumptions)
1. ነጻ የሕሊና ግምት (permissive presumption)
2. የሚስተባበል የሕሊና ግምት (rebuttable presumption)
3. የማይስተባበል የሕሊና ግምት (irrebuttable/ conclusive presumption)
1.ነጻ የሕሊና ግምት (permissive presumption)
-የዚህ ዓይነቱ ነጻ የሆነ ወይም አስገዳጅ ያልሆነ የሕሊና ግምት ፍ/ቤቱ የአንድን አከራካሪ ፍሬ ነገር መኖርና አለመኖር በራሱ ነጻ አስተሳሰብ ግምት እንዲወስድ ሥልጣን የሚሰጥ ነዉ፡፡
-የዚህ አይነቱ የሕሊና ግምት ፍርድ ቤቱ አንድ መነሻ የሚሆን መሠረታዊ ፍሬ ነገር በቅድሚያ ከተረጋገጠ አከራካሪ የሆነዉን ተከታዩን ፍሬ ነገር እንደተረጋገጠ ሊቆጥረዉ ይችላል፡፡
-ፍ/ቤቱ ከፈለገ ደግሞ ማስረጃ እንዲቀርብ ለማዘዝ ይችላል
ለምሳሌ፡- የፍ/ብ/ሕ/ቁ 22
አንድ ሰዉ በሐኪም ምርመራ ለመመርመር እንቢ ያለ እንደሆነ ዳኞች ተመርመሮ ሊገኝበት ይችላል ተብሎ የተገመተዉ ነገር እንዳለበት ያሕል ሊቆጥሩት ይችላሉ፡፡
ሕድአት ጌታቸዉ
የካቲት/2014 ዓ.ም

Comments

Be the first to add a comment