👉የቀድሞ ቢሊየነር አሁን ላይ ደሞዝተኛ ሆነዋል

በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ለ30 ዓመታት ያህል በግንባር ቀደምነት ሲንቀሳቀስ የነበረው የአኪር ኮንስትራክሽን መስራችና የቀድሞ ባለቤት አቶ አወጣኸኝ ኪሮስ ከቢሊየን ብር በላይ ካፒታል እና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞችን ከማስተዳደር ወደ ተቀጣሪ ደመወዘኛነት መሸጋገራቸውን ከአርትስ ቴሌቪዥን ሰምተናል።

ድርጅታቸው በወቅቱ በነበሩ የመንግስት ኃላፊዎች ውሳኔ አዳዲስ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች እንዳያገኝ በመከልከሉ እና በ2009 ዓ.ም በደባርቅ በነበረው ካምፓቸው ላይ በደረሰ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ምክንያት ለከፍተኛ የባንክ እዳና የሰራተኞች ውዝፍ እዳ ተዳረገ።

​ይህንን ፈተና ለመወጣት ሲሉ አቶ አወጣኸኝ የስላሳ ዓመት ልፋታቸውንና ክብራቸውን በመተው ድርጅቱን አዳዲስ ገዢዎች እንዲረከቡት አድርገው ነበር።

ሆኖም አዳዲሶቹ ባለቤቶች የተስማሙበትን እዳ ባለመክፈላቸው ምክንያት ላለፉት ሰባት ዓመታት በሕግ ሲከራከሩ ቆይተዋል።

በእነዚህ የውጣ ውረድ ዓመታት ውስጥ አቶ አወጣኸኝ የነበራቸውን ሀብት አጥተው የቀድሞ ተፎካካሪያቸው በነበረው ሌላ የኮንስትራክሽን ድርጅት ሠራተኛ ሆነው ሲሰሩ ቆይተዋል።

​አሁን ላይ ለሰባት ዓመታት ሲካሄድ የቆየው የሕግ ክርክር ፍጻሜ አግኝቶ ፍርድ ቤቱ የአኪር ኮንስትራክሽን አክሲዮኖች በሐራጅ እንዲሸጡ የመጨረሻ ውሳኔ አስተላልፏል።

ይህ የፍርድቤት ሂደት አቶ አወጣኸኝን ወደ ቀድሞ ህይወት የሚመልስ አዲስ ጅማሮ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

በያፌት ገ/ህይወት

@etconp

Comments

Be the first to add a comment