👉"ልምድ በሌለው ኮንትራክተር ምክንያት መንግስት 450 ሚሊዮን ዩሮ ካሳ ከፍሏል"

ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ

🚧በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ላይ ስለሀይድሮ ኤሌክትሪክ ምንም አይነት ልምድ በሌለው ኮንትራክተር ምክንያት መንግስት 450 ሚሊዮን ዩሮ ካሳ ከፍሏል ሲሉ የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ገለጹ።

💫የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ከጋዜጣ ፕላስ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ ፕሮጀክቱን ረጅም ጊዜ ያቆየው እና ትልቅ መሰናክል የተፈጠረው ምንም አይነት ልምድ የሌለው ኮንትራክተር ትልቁንና ውስብስቡን የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ስራ እንዲሰራ መደረጉ ነው።

💫የበለስ ሀይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮጀክትን ለመገንባት የፈጀው 460 ሚሊየን ዩሮ መሆኑን ለማሳያነት ያነሱት ኢንጂነር ክፍሌ፤ ህዳሴ ግድብ ላይ ልምድ የሌለው ኮንትራክተር እንዲሠራ መደረጉ አንድን የኤሌክትሪክ ኃይል ጣቢያ መገንባት የሚያስችል ኪሳራ አድርሷል ብለዋል፡፡

💫ኮንትራቱ ከተፈረመ ከሁለት ወራት በኋላ የሲቪል ስራውን የወሰደው ኮንትራክተር በግድቡ መሰረት ላይ ልል ድንጋይ እንዳጋጠመው እና ድንጋዩን አውጥቶ መሠረቱን በኮንክሪት ለመሙላት ተጨማሪ ሶስት ዓመት እንደሚወስድበት ገልጾ እንደነበር ስራ አስኪያጁ አስታውሰዋል፡፡

💫የሀገር ውስጥ ኮንትራክተር በዘርፉ እንዲበቃ፤ በጥሩ እሳቤ የፕሮጀክቱን ግንባታ ቢጀምርም ነገር ግን መንግስት በቂ ዝግጅት ሳይደረግ ለኮንትራክተሩ እንዲሰጥ መወሰኑ ትልቅ ስህተት እንደነበር በቁጭት ተናግረዋል፡፡

💫ፕሮጀክቱ እንደተጀመረ አካባቢ ህጻናት ቁርሳቸውን ትተው፤ እናቶች ከመቀነታቸው ያላቸውን ገንዘብ ሰጥተው እንዲሁም ህዝቡ በአጠቃላይ ተሳትፎ ሲሰራ እንደነበር ያወሱት ሥራ አስኪያጁ፤ በቂ መረጃ ለህዝቡ ባለመሰጠቱ የኢትዮጵያዊያንን ሞራል በእጅጉ እንደጎዳ ጠቁመዋል፡፡

💫ሀገራዊ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፕሮጀክቱ የገጠሙትን ችግሮች በመገምገም እና የኮንትራት ይዘቱ እንዲቀየር በማድረጋቸው ፕሮጀክቱ ነብስ መዝራት መቻሉን ተናግረዋል፡፡

⏺መንግስት ከቦርድ ጀምሮ እስከ መጨረሻው ድረስ ሪፎርም ካደረገ በኋላ የፕሮጀክቱ ስራ ሲጀመር ስራውን ለማስቆም የተፋሰሱ ሀገራት የተልዕኮ ጦርነት መጀመራቸውን ኢንጂነር ክፍሌ ገልጸዋል፡፡

🏷በአጠቃላይ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በመንግስትና በህዝብ ርብርብ በርካታ መሰናክሎችን በማለፍ ለመጠናቀቅ እንደበቃ ግልጸዋል፡፡

Via Gazette Plus

@etconp

1 comment

በውሸት ፣ በተንኮል ፣ በስልጣን ጥም ፣ መረጃን በማጥፋትና በማዛባት ህዝብን ለመዋሸት እና የአባይ ግድብን እውን ያደረጉትን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ እና ኢ/ር ስመኘው በቀለን ስም ማጥፋት ፈፅሞ አይቻልም።
ህዝቡ ማን እንደሚሰራ እና ማን ሌባ እና ውሸታም እንደሆነ ጥንቅቅ አድርጎ ያውቃል። አውቋል። አትድከሙ!
አባይ ግድብ ሲነሳ ክቡር መለስ ዜናዊ በደማቅ ይነሳል!