👉የምህንድስናው ዘርፍ ግዙፉ ሲካ አቢሲኒያ የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን አብዮት የሚቀይሩ አራት አዳዲስ የሀገር ውስጥ ምርቶችን አስተዋወቀ

💫በሀገራችን የኮንስትራክሽን ዘርፍ ግንባር ቀደም ስም ያለው ሲካ አቢሲኒያ (Sika Abyssinia)፣ የዘርፉን ተግዳሮቶች በዘላቂነት ለመቅረፍ የሚያስችሉና ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ የተመረቱ አራት አዳዲስ እጅግ ዘመናዊ ምርቶቹን ባለፈው ቅዳሜ ወሎ ሰፈር በሚገኘው ቤስትዌስተርን ፕላስ ሆቴል ባካሄደው ደማቅ መርሃ-ግብር ላይ አስተዋውቋል።

የግንባታ ጥራትን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ እነዚህ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የግንባታን ጥራት፣ ጥንካሬና ውበት ደረጃ ከማሳደጋቸውም በላይ ለኢንዱስትሪው አዲስ ተስፋ ይዘው ብቅ ብለዋል።

የስዊዘርላንዱ ግዙፍ ተቋም Sika AG እህት ኩባንያ የሆነው ሲካ አቢሲኒያ፣ በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኬሚካሎች ማምረቻ ፋብሪካውን በመክፈት ጥራት ያላቸውን ምርቶች በአገር ውስጥ እያመረተ ይገኛል።

በሀገራችን የግንባታ ታሪክ ውስጥ በተለይም የውሃ ስርገት (Water Leakage)፣ የግድግዳ መሰነጣጠቅና መላላጥ፣ እንዲሁም የቀለም መበላሸት ለህንጻ ባለቤቶችና ለኮንትራክተሮች ዋነኛ ራስ ምታት ሆነው ቆይተዋል።

እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ቀደም ሲል ውድ የሆኑ ኬሚካሎችን ከውጭ ሀገር በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ማስገባት የግድ ነበር።

ሲካ አቢሲኒያ እነዚህን አራት አዳዲስ ምርቶች በሀገር ውስጥ ማምረቱ በኮንስትራክሽን ዘርፉ ላይ የሚከተሉትን ትልቅ ጥቅሞች ያስገኛል፦

• የውጭ ምንዛሬን ያድናል፦

ቀደም ሲል ከውጭ ይገቡ የነበሩ ጥራት ያላቸውን ኬሚካሎች በሀገር ውስጥ ምርት መተካት ችሏል።

• ወጪን ይቀንሳል፦

የግንባታ ባለሙያዎችና አልሚዎች ጥራቱን የጠበቀ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ በአቅራቢያቸው እንዲያገኙ ያደርጋል።

• ለሀገር በቀል ግንባታ ዋስትና ይሰጣል፦

የኢትዮጵያን የአየር ንብረትና የግንባታ ሁኔታዎች ባገናዘበ መልኩ የተሰሩ በመሆናቸው አስተማማኝነታቸው ከፍተኛ ነው።

በዕለቱ ለገበያ የቀረቡት ምርቶች በዋናነት በህንጻ ግንባታ ላይ የሚከሰቱ አራት አንገብጋቢ ችግሮችን የሚፈቱ ናቸው፦

1. የአርማታ ውሃ ስርገትን ሙሉ በሙሉ የሚያስቀር ፈሳሽ

የመጀመሪያው ምርት በአርማታ (ኮንክሪት) ስራ ወቅት አብሮ የሚቀላቀል ፈሳሽ ኬሚካል ሲሆን፣ በ5 እና በ20 ሊትር ተለይቶ ተዘጋጅቷል።

ይህ ምርት በተለይ ለቤት መሰረት፣ ለፎቅ ወለል፣ ለመዋኛ ገንዳ፣ ለውሃ ማጠራቀሚያዎችና ለዋሻዎች ፍፁም ተመራጭ ነው። አርማታው ውሃ እንዳያሳልፍ ከፍተኛ ጥበቃ ከማድረጉም በላይ፣ ግንባታው በጨው ውሃና በኢንዱስትሪ ኬሚካሎች እንዳይጎዳ የመከላከል ልዩ አቅም አለው።

2. የቀለም ፍጆታን የሚቀንስና ውሃ የማይበሳው የግድግዳ ፑቲ

በ20 ኪ.ግ ታሽጎ የቀረበው ሁለተኛው ምርት፣ ለውስጥም ሆነ ለውጭ ግድግዳ እና ለኮርኒስ ስራዎች ለስላሳ ገጽታን የሚሰጥ የሲሚንቶ ባህሪ ያለው ፑቲ ነው።

ምርቱ በቀላሉ ከውሃ ጋር ብቻ ተደባልቆ የሚዘጋጅ ሲሆን፣ ግድግዳ ላይ የመጣበቅ ኃይሉ ከፍተኛ በመሆኑ ለረጅም ጊዜ ሳይላላጥ ይቆያል። ከሁሉም በላይ ያለ ምንም ቻክ ቀጥታ ለቀለም ስራ የሚያመች በመሆኑ የቀለም ፍጆታንና ወጪን በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ ይረዳል።

3. መሰነጣጠቅንና መላላጥን የሚከላከል የልስን ዱቄት

ይህ ምርት ለቤት ውስጥና ውጭ የልስን ስራዎች የሚጠቅም ሲሆን፣ ከብሎኬት በላይ ለብቻው እንደ ማጠናቀቂያ ልስን ወይም ከማስዋቢያ ስራዎች በፊት እንደ ማደላደያ ሆኖ ያገለግላል።

እርጥበት ሰርጎ እንዳይገባ የመከላከል አቅም ስላለው የቀለምን እድሜ ያረዝማል።

በተለምዶ በሳይት ላይ በእጅ ከሚዘጋጅ ልስን ጋር ሲነጻጸር ግድግዳ ላይ የመጣበቅ ኃይሉ እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ ግድግዳ በቀላሉ እንዳይሰነጣጠቅ ያደርጋል።

4. የኮንክሪትና ሲሚንቶ ክፍሎችን መልሶ የሚያጣብቅ ፈሳሽ

አራተኛው ምርት ከውሃ፣ አሸዋ እና ሲሚንቶ ጋር ተዋህዶ በአርማታ እና በሌሎች በሲሚንቶ የተሰሩ ግንባታዎችን እርስ በእርስ ለማጣበቅ የሚያገለግል ፈሳሽ ነው።

በተለይም ለግድግዳና ወለል ልስን፣ ለታይል ንጣፍ፣ ለድንጋይ ርብራብ ስራ እንዲሁም ለተቦጨቀና ለተጎዳ የአርማታ ጥገና ፍፁም ተስማሚ ነው። የኮንክሪትን ጥንካሬና የመለጠጥ አቅም የሚያሻሽል ሲሆን፣ መሰነጣጠቅንና መላላጥን ያስቀራል።

በማስመረቂያ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙ የዘርፉ መሃንዲሶችና ባለሙያዎች እንደገለጹት፤ እነዚህ የሲካ አቢሲኒያ ምርቶች በሀገር ውስጥ መመረታቸው በግንባታ ወቅት የሚባክነውን ጊዜና ወጪ ከመቀነሱም በላይ፣ በሀገራችን እየተገነቡ ያሉ ዘመናዊ ህንጻዎች የውጭውን ዓለም ደረጃ የጠበቁና ለረጅም ዘመናት የሚጸኑ እንዲሆኑ ትልቅ እገዛ ያደርጋሉ።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment