👉የኮንክሪት የውሃ ማፍሰሻ ቦይ (Concrete Roof Gutter) ውሃ እንዳያስተላልፍ የሚደረጉ ዋና ዋና ጥንቃቄዎች!

​በምስሉ ላይ እንደምናየው በቆርቆሮው እና በፓራፔት ግንቡ መካከል የኮንክሪት ቦይ (Concrete Gutter) ተሰርቷል። ይህ ቦታ በህንፃዎች ላይ ከፍተኛ የውሃ ሰርጎ የመግባት (Water Leakage) አደጋ ከሚፈጠርባቸው ቦታዎች አንዱ ነው።

​በኮንክሪት ጋተር ስራ ወቅት ሊረሱ የማይገባቸው ነጥቦች፦

1. ​Proper Slope/Fall: ኮንክሪቱ ውሃ እንዳያቁር ቢያንስ 1% እስከ 2% ተዳፋትነት (Slope towards downspout) ሊኖረው ይገባል።

2. ​Waterproofing Membrane: በኮንክሪት ቦዩ ላይ ጥራት ያለው የውሃ መከላከያ (App Waterproofing Membrane / Elastomeric Coating) መቀባት/መንጠፍ።

3. ​Flashing & Overlap: በቆርቆሮው እና በጋተሩ መካከል ያለው መጋጠሚያ ላይ ብረታዊ ፍላሽንግ (Metal Flashing) ገብቶ በቂ Overlap መኖሩን ማረጋገጥ።

​በእርስዎ ሳይት ላይ ለኮንክሪት ጋተር ውሃ መከላከያ Crystalline Coating ይመርጣሉ ወይስ Bituminous Membrane?

@etconp

Comments

Be the first to add a comment