👉የዓለማችን አምስቱ ውብ
ከተሞች

🚧በአሁኑ ወቀት በበርካታ የአለማችን በከተሞች ላይ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡

🚧እነዚህ ተግባራትም ከተሞችን ከብክለትና መሰል ችግሮች በመታደግ አረንጓዴ እና ጤናማ የሆኑ ከተሞችን ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ዋነኛ አላማ ያደረገ ነው፡፡

🚧እኛም በአረንጓዴ ልማት ስትራተጂ ውጤታማ ስራ የሰሩና ለሌሎች የአለማችን ከተሞች ተሞክሮ መሆን የቻሉ 5 ከተሞችን በደረጃ ልናስተዋውቃችሁ ወደናል::

📌በአለማችን የአረንጓዴ ልማት ዘርፍ ውጤታማ ስራ ከሰሩ ከተሞች መካከል በ5ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው በአሜሪካን ሀገር የምትገኘው ሳንፍራንሲስኮ ከተማ ናት ከተማዋ በዘርፉ ከሰራቻቸው ስራዎች መካከልም በሀገሪቱ ከሚገኙ ከተሞች በፅዳት፣ በአረንጓዴ ልማትና በኤሌትሪክ ሀይል የሚሰሩ የሀይል አማራጮችን በመጠቀም ተጠቃሽ ናቸው ይህም ጠንካራ ህግ ተፈፃሚ ከማድረግ ባሻገር ህብረተሰቡ ይህን ለመተግበር በአመለካከት የተለወጠ መሆኑ ነው ባጠቃላይ በከተማዋ 40 በመቶ የሚሆነው ክፍልም በአረንጓዴ ስፍራ የተሸፈነ ነው::

📌በአረንጓዴ ልማት ስትራተጂ በ4ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ከተማ በእስያ አህጉር የምትገኘው ሲንጋፖር ከተማ ናት ይህች ከተማ ሙሉ ለሙሉ በሚያስብል መልኩ መሰረታዊ የከተማ ልማት ጥያቄዎችን መፍታት የቻለች ከተማ ናት በከተሞቻቸው የሚሰሩ ስራዎች ለመጠበቅ ጠንካራ ህግ ከማርቀቅ ጎን ለጎን በአረንጓዴ ልማትና በአካባቢ ጥበቃ በተለይ ደረቅ እና ፍሳሽ ቆሻሻን መልሶ አገልግሎት ላይ እንዲውል በማድረግ ረገድ ለሌሎች ከተሞች ተምሳሌት ሆነዋል፡፡
*በከተማዋ ወደ ሰላሳ የሚጠጉት አረንጓዴ የህዝብ ፓርኮችም ከተማዋ ለአረንጓዴ ልማት የሰጠችውን ትኩረት ማሳያዎች ሲሆኑ በከተማዋ ሰፋፊ ጥብቅ ደኖችም ይገኛሉ፡፡
*በቅርቡም ከተማዋ ተግባራዊ እድርጋ ውጤት ባስመዘገበችባቸው ስራዎች በዩኒስኮ የአለም ከተሞች ተምሳሌት በመሆን ያገኘችው ሽልማት ተጠቃሽ ነው፡፡

📌በ3ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ከተማ የብራዚሏ ኩሪቲባ ከተማ ናት ይህች ከተማ ከአለማችን ከተሞች መካከል በአረንጓዴነቷ የሶስተኛ ደረጃን ይዛለች በከተማው ከሚወጣው ቆሻሻም 70 በሞቶውን ለመልሶ አገልግሎት ማዋል ችለዋል፡፡ *በርካታ ጥብቅ ደኖች በከተማዋ መኖራቸው እና ዘመናዊና ቀላል የአውቶብስ የትራንስፖርት ተግባራዊ ማድረጋቸው ከስኬቶቻቸው መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

📌በ2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ከተማ ደግሞ የፊንላዷ ሄልሲንኪ ናት ይህች ከተማ በአካባቢ ጥበቃና በ መሰረተ ልማት ዘርፎች ላይ የሚታዩ ችግሮችን በአግባቡ በመቅረፍ ብሎም ለኪነ ህንፃ እና ሁለንተናዊ ለሆነ የከተማ ውበት ልዩ ትኩረት በመስጠት ውጤታማ ስራ ሰርተዋል በዚህም በአለማችን እጅግ በጣም ማራኪ ከሚባሉ ከተሞች ቀዳሚ ለመሆን ችለዋል ለዚህም እንደማሳያ የከተማዋ አብዛኛው ስፍራ በማራኪ አረንጉዴ ስፍራዎች ከመሸፈኑ ጎን ለጎን ከተማቸውን ማራኪ በሆነ የስነ ህንፃ ዲዛይን ዉብ ማድረግ በመቻላቸው ነው፡፡

📌በመጨረሻም በዘርፉ በ1ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ከተማ የዴንማርኳ ኮፐንሀገን ናት ይህች ከተማ ከአለማችን ከተሞች
በቀዳሚነት የካርቦን ልቀት በመቀነስ አረንጓዴ፣ ውብና ለኑሮ ተስማሚ ከተማ መቀለስ ችላለች፡፡ *በተጎናጸፉት ስኬትም በከተማ ልማት ዘርፍ አንከን አይወጣላቸውም እየተባሉ ይወደሳሉ፡፡
*ጥናቶች እንደሚጠቁሙትም ይህች ከተማ በአለማችንም እጅግ በጣም ደስተኛ ዜጎች ከሚኖሩባቸው ከተሞች መካከል በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ ከተሞች ተርታ ተሰልፋለች፡፡

🚧እኛም ከነዚህ ከተሞች በርካታ ተሞክሮዎች መቅሰም ይኖርብናል እነዚህ ከተሞች ዛሬ የደረሱበት ስኬት ጠንካራ ህጎችን ማርቀቅና ተግባራዊ ማድረግ ወይም ደግሞ ከተሞቹ በመደቡት የገንዘብ አቅም እንዳይመስሎ በነዋሪዎቻቸው ዘንድ በአውንታዊና ቅን በሆነ አመለካከት የተቃኘ የአስተሳሰብ ልእልና መገንባት በመቻላቸው እንጂ፡፡

➡️በአረንጓዴ እና ዉብ ስፍራዎች የሚኖሩ ዜጎችም ደስተኛ ከመሆናቸውም ባሻገር አዳዲስ ሀሳቦችን በማፍለቅ የዜጎችን ህይወት መቀየር ይችላሉ፡፡

➡️በሀገራችን ከተሞችም በቅርቡ የተጀመሩ የአረንጓዴ ልማት ስራዎች አሁን ባለው ተነሳሽነት ማስቀጠል ከቻልን በአለማችን ተጠቃሽ ከሆኑ አረንጓዴ እና ዉብ ከተሞች መካከል ከተሞቻችንን ለማስጠራት የሚያግደን ነገር አይኖርም።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment