👉ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ መጠናቀቅ እንዳለባቸው ተገለጸ

በመንግስት ወጭ የሚገነቡ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ መጠናቀቅ እንዳለባቸው ተገልጸ፡፡

የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሎ ጫልቱ ሳኒ በፈዴራል መንግስት ህንጻ ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አማካኝነት እየተገነባ ያለውን የሰነዶች ማረጋገጫና መዝገባ አገልግሎት የህንጻ ግንባታ ፕሮጀከት አፈጸጸም አስመልክቶ  ውይይት አካሂደዋል ፡፡

ፕሮጀክቱ እ.ኤ. አቆጣጠር መስከረም 26 ቀን 2020 ላይ በ1ነጥብ 4ቢሊዮን ብር የተጀመረ ሲሆን በሚቀጥለው መጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ እንደምሆን በውይይት ተገልጿል፡፡

ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ እና ለሚፈለገው አላማ አገልግሎት ላይ እንድውል የስራ አቅጣጫ የሰጡት የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሎ ጫልቱ ሳኒ  ስራው በተለያዩ ምክኒያቶች መጓተቱን በመረዳትና በማረም አላስፈላጊ ሰበቦችን ትተን የሚጨበጥ ስራን በማሳየት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተባብረው፣ ተረዳድተው፣ ተቀናጅተው ፕሮጀክቱን ከፍጻሜ ማድረስ እንደምገባ አሳስበዋል

Via መልሚ

@etconp

Comments

Be the first to add a comment