የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
1. የዉል ህግ ይርጋ
የይረጋ ጊዜን የሚመለከት የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1845 ህግ በሌላ አኳኋን ካልወሰነ በቀር ዉሉ እንዲፈፀም ወይም ካለመፈፀሙ የተነሳ ስለሚደረስ ጉዳት ወይም ዉሉ እንዲፈርስ የመጠየቅ መብት በ10 ዓመት ይርጋ ይቀራል ሲል ደንግጎ ይገኛል፡፡
2. ከዉል ዉጪ ኃላፊነት ይርጋ
ከዉል ዉጪ ኃላፊነት የዉል ግንኙነት ሳይኖር ወይም ዉል ላይ ባለተመሰረተ ግንኙነት በአንድ ሰዉ ጥቅም ወይም መብት ጉዳት ሲደርስ ለዚህ ጉዳት ኃላፊነት የሚደርስበትን አካል የሚለይና ጉዳት በካሳ መልክ እንዲስተካከል የሚያደርግ ሕግ ነዉ፡ እንዲሁም ጥፋት ሳይኖር የሚመጣ ኃላፊነትን ፣በሌላ ሰዉ ተግባር ኃላፊነትን እና በጥፋት ላይ የተመሰረተ ኃላፈነትን የሚያጠቃልል ሲሆን የኃላፊነቱ ምንጮች ተብለዉ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2027 ተደንግጓል፡፡
የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2143 ተበዳዩ ክስ ማቅረብ የሚችለዉ ካሳ የሚጠየቅበት ጉዳቱ ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 2 ዓመት ድረስ ሲሆን ጉዳቱ በወንጀል የሚያስቀጣ ሆኖ የይርጋ ዘመኑ ርዝመት የበለጠ እንደሆነ የካሳዉ ጉዳይ ክስ የይርጋ ዘመን ልክ በዚሁ መሰረት ይሆናል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2065 መሰረት አንድ ሰዉ በባለይዞታነቴ ወይም በይርጋ ደንብ መከሰስ ቀርቶልኛል ብሎ ቢከራከር ጥፋተኛ አይደለም በሚል ተደንግጎ ይገኛል፡፡
ፌናን ተጊበሉ
ጥር 2/2014 ዓ.ም
Comments
Be the first to add a comment