የኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪነትና ውጤታማነት ለማረጋገጥ ቴክኖሎጂው የጎላ ሚና አለው ተባለ

ሴነ 4 ቀን 2018 አምቦ

ይህ የተባለው ኢንሰቲትዩቱ ከአሮሚያ ኮንስትራክሽንና ባለስልጣንና አምቦ ዩንቨርሲቲ ጋር በቅንጅት በግንባታ መረጃ ሞዴሊንግ (Building information Modeling/BIM )ቴክኖሎጂ  ላይ ያተኮረ ስልጠና መስጠት በተጀመረበት ወቅት ነው።

ይህንንም ያሉት በስልጠና መድረኩ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ኢ/ር ሌንሣ መርጋ ናቸው።

በንግግራቸውም ኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪና ውጤታማ ማድረግ  ከተፈለገ ዘርፉን በቴክኖሎጂ  ማስደገፍ ወሳኝ መሆኑን እና የBIM ቴክኖሎጅም ለዚህ የጎላ ሚና እንዳለው ተናግሯል።

ስልጠናውም ተከታታይነት ባለው መልኩ እየተሰጠ ያለውም ይህንን በመገንዘብ እንደሆነ በመጠቆም።

የእንኳን ደና መጣችሁ መልክት ያስተላለፉት እና ስልጠናውን መስጠት የሚያስችል ቅድሜ ዝግጅት መጠናቀቁ ያስገነዘቡት ደግሞ የአምቦ ዩንቨርሲቲ ተወካይ ኢ/ር ወዬሣ አራርሳ ናቸው።

ዩንቨርሲቲውም መሠል ስልጠናዎችን ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት የመስጠት ልምድ ያለው መሆኑን በመጥቀስ፣ ሰልጣኙም የሚፈለገውን እውቀት ጨብጦ እንደሚወጣ ተስፋቸውን ተናግሯል።

ኢንስቲትዩቱም ኢንዱስትሪው የሚጠበቅበትን ሚና መወጣት እንድችል የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እና ችግር ፈች ጥናትና ምርምሮችን እያከናወነ እንደምገኝ እና ይህም ስልጠና በተከታታይነት እየተሰጠ መሆኑን የጠቀሱት ደግሞ ወ/ሮ ፋናዬ ንጉሤ ናቸው።

ስልጠናውም ለተከታታይ 16 ቀናት የሚሰጥ ሲሆን፣  ከ4ቱም ወለጋ ዞኖች፣ ከምዕራብ ሸዋ፣ ጅማና መሠል ዞኖች የተውጣጡ ሰልጣኞች በስልጠናው ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

መረጃው የኢንስቲትዩቱ ነው

@etconp

Comments

Be the first to add a comment