🌟ስለ ኤቫኮኔት

Www.Evaconet.com (Eva Construction Network Market) በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ የግብአት አቅርቦትን ለማቀላጠፍና በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማደራጀት የተቋቋመ ግንባር ቀደም የመስመር ላይ የገበያ መድረክ (Digital Marketplace) ነው።

ይህ ዲጂታል ፕላትፎርም በሀገሪቱ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ የሚያከናውነው ሥራ፣ ለሀገር ያለው ፋይዳ እና አጠቃቀሙ እንዴት ነው? ለሚሉ ጥያቄዎች እንደሚከተለው

1. በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ግብአት አቅርቦት ላይ የሚሠራው ሥራ ምንድ ነው?
ኢቫኮኔት (Evaconet) ገዢዎችን (ግለሰቦችን፣ ተቋራጮችን እና መሐንዲሶችን) ከግንባታ እቃ አቅራቢዎች፣ አምራቾች እና ነጋዴዎች ጋር የሚያገናኝ ድረ-ገጽ ነው።

የሚከተሉትን ዋና ዋና የግብአት ዘርፎች ይሸፍናል፦

የመሠረታዊ የግንባታ እቃዎች፦ ሲሚንቶ፣ ብረታ ብረት (የኮንክሪት ብረት/Rebar)፣ አሸዋ፣ ጠጠር፣ ጡቦች እና የጣሪያ ቆርቆሮዎች።

የኤሌክትሪክ እና የብርሃን እቃዎች፦ ኬብሎች፣ መብራቶች፣ ሶኬቶች እና የኃይል ማከፋፈያዎች።

የቧንቧ እና የውሃ ሥራ እቃዎች፦ የውሃ ታንከሮች፣ የቧንቧ ዕቃዎች እና ማቀንቀኛዎች።

የጌጣጌጥ (Finishing) እቃዎች፦ የቤት ውስጥ እና የውጭ ቀለሞች፣ የጣሪያ፣ የወለል እና የግንብ ማጠናቀቂያ እቃዎች (እንደ ግራናይት እና ሴራሚክስ ያሉ)።

ታዳሽ የኃይል ቴክኖሎጂዎች፦ የሶላር ፓነሎች፣ ሶላር ጀነሬተሮች፣ የውሃ ማሞቂያዎች የውሀ ፓምፖች ፣ የሻወርቤት እቃዎች ፣ ፣ የቤት ውስጥ ማንኛውም መጠቀሚያዎች ወዘተርፈና
ለአሸዋ ለጠጠር ለብሎኬት አምራቾች እንዲሁም ተጠቃሚዎች የተለያዩ ባለሙያዎችን የማሽን ክራዮችን ቢፈልጉ በቀላሉ የሚያገኙበት ፕላትፎርም ስለሆነ በነጻ እየተመዘገባችሁ ተጠቀሙ

2. ኤቫኮኔት ዲጂታል ፕላትፎርም ለሀገር ያለው ፋይዳ ምንድ ነው? ለኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፍ እና ለኢኮኖሚው የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፦

👉ግልጽነትን መፍጠር እና ዋጋን ማወዳደር፦ ደንበኞች የተለያዩ አቅራቢዎችን ዋጋ በአንድ ቦታ ላይ ሆነው በማወዳደር ኪስ የሚመጥንና  ትክክለኛ ግዢ እንዲፈጽሙ ያስችላል።

👉የኮንስትራክሽን ገበያውን ዲጂታላይዝ ማድረግ፦ ባህላዊና አስቸጋሪ የነበረውን የግንባታ እቃ ፍለጋና ግብይት በቴክኖሎጂ በማዘመን ጊዜንና ጉልበትን ይቆጥባል።

👉ታማኝ አቅራቢዎችን ማስተዋወቅ፦ የተረጋገጡ (Verified Suppliers) አቅራቢዎችን በመጠቀም ተጠቃሚዎች ሕገ-ወጥ ንግድና አጭበርባሪዎች እንዳይጠቁ ይረዳል። እንዲሁም አነስተኛና መካከለኛ አቅራቢዎች ገበያቸውን እንዲያሰፉ ዕድል ይሰጣል። ተጠቀሙት

👉የግንባታ መዘግየትን መቀነስ፦ አስፈላጊ የሆኑ እቃዎችን ካሉበት ቦታ በፍጥነት በማግኘትና አማራጮችን በማሳየት በፕሮጀክቶች ላይ የሚደርሰውን የጊዜ መዘግየት ይቀንሳል።

3. አጠቃቀሙስ ( ፕላትፎርሙን እንዴት መጠቀም ይቻላል?)

ኤቫኮኔት ለመጠቀም ለተጠቃሚዎች የተስተካከለና ቀላልና በአራት ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን (User-friendly) በሆነ መንገድ የተዘጋጀ ነው፦
* ድረ-ገጹን መጎብኘት፦ በመጀመሪያ በጎግል በክሮም በኦፔራ ሚመቻችሁ ብሮውዘር Evaconet.com ብላችሁ [www.evaconet.com](https://www.evaconet.com) በመክፈት  የኮንስትራክሽን ማቴሪያል ነጋዴዎች በራሳችሁ የምታስተዳድሩት ፖርታል ስለሆነ የራሳችሁን ሚስጥራዊ ኮድ ፈጥሮ በመመዝገብ ሎጊን ብሎ ምርትና ድርጅታችሁን በቀላሉ በማስተዋወቅ ወቅታዊ የመሸጫ ዋጋ እየለጠፉ መጠቀም ዋጋ ስትቀይሩም ወዲያውኑ መቀየር እና ተጠቃሚዎች(ገዢዎች) ወደ ኤቫኮኔት በመግባት በያላችሁበት ቦታ የምትፈልጉትን ግዙ።

👉በቀላሉ ምርቶችን መፈለግ፦ በሚፈልጉት የቁሳቁስ ምድብ (ለምሳሌ፦ ሲሚንቶ፣ ብረት፣ ኤሌክትሪክ እቃዎች ወዘተ) በመግባት የሚፈልጉትን እቃ መፈለግ።
👉ዋጋዎችንና ጥራትን ማወዳደር፦ በተለያዩ አቅራቢዎች የቀረቡትን የምርት አይነቶች፣ ዋጋዎች እና ዝርዝር መግለጫዎች ማወዳደር።

ከአቅራቢዎች ጋር በቀጥታ መገናኘት፦ የሚፈልጉትን እቃ ሲያገኙ በቀጥታ ድረ-ገጹ ላይ ካሉ አቅራቢዎች ጋር በመደወል ወይም የመልእክት አማራጮችን በመጠቀም ግይቱን ማጠናቀቅ ይቻላል።

በአጠቃላይ ኢቫኮኔት በኢትዮጵያ እየተስፋፋ የመጣውን የዲጂታል ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በመቀላቀል የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪውን ዘመናዊና ቀልጣፋ ለማድረግ ትልቅ ሚና እየተጫወተ ያለ መድረክ ነው።

ማሳሰቢያ በመላው አለም ያለ ነጋዴ ባለሙያ የማሽንና የጭነት አከራይ እንድትመዘገቡ እና ሎጊን ብላችሁ ምርታችሁን እንድታስተዋውቁ አደራ እላለሁ።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment