👉የኮንስትራክሽን ኮንትራክት አስተዳዳሪ (Construction Contract Administrator / Contract Management Expert) ዋና ኃላፊነቱና የስራ ድርሻው ምንድን ነው?

⬇️የኮንስትራክሽን ኮንትራክት አስተዳዳሪ ዋናVኃላፊነቱ የግንባታ ውል ከመዘጋጀት እስከ ፕሮጀክቱ መጠናቀቅ ድረስ ውሉ በትክክል እንዲፈጸም ማስተዳደር ነው።

   🔆ዋና ዋና የስራ ድርሻዎች
     ---------——------—----
   ✏️የኮንትራት ሰነዶችን ማዘጋጀትና መገምገም።
   ✏️የጨረታ ሂደትን መደገፍ (Tender Administration)።
   ✏️ከተቋራጩ ጋር የተፈረመውን ውል መከታተል።
   ✏️የስራ ለውጦችን (Variation Orders) ማስተዳደር።
   ✏️የክፍያ ማመልከቻዎችን መመርመርና ማረጋገጥ።
  ✏️የጊዜ ማራዘሚያ (Extension of Time) ጥያቄዎችን መገምገም።
   ✏️የውል ግጭቶችንና ክርክሮችን መፍታት።
   ✏️የፕሮጀክት ሪፖርቶችን ማዘጋጀት።
   ✏️የውል ህጎችን፣ መመሪያዎችንና ደንቦችን ማስከበር።
   ✏️ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ የመጨረሻ ሂሳብ (Final Account) ማዘጋጀትና ውሉን መዝጋት።

  🏛አብሮ የሚሰራቸው
   -----------—-----—---
    🎤የፕሮጀክት ማኔጀር
    🎤የሳይት ኢንጅነር
   🎤የቁጥር መሐንዲስ (Quantity Surveyor)
   🎤የግዥ ባለሙያ
   🎤የሕግ አማካሪ
   🎤ተቋራጭ (Contractor)
   🎤አማካሪ (Consultant)
   🎤የፕሮጀክት ባለቤት (Client)

🚥ሊያውቃቸው የሚገቡ ክህሎቶች
   -----—--------------—
         ✏️የኮንትራት ህግ
         ✏️የግንባታ አስተዳደር
         ✏️የዋጋ ግምትና ክፍያ
         ✏️ድርድር (Negotiation)
         ✏️ሪፖርት ጽሑፍ
         ✏️የፕሮጀክት መርሃ ግብር አስተዳደር

🌟በአጭሩ፦ የኮንስትራክሽን ኮንትራክት አስተዳዳሪ የፕሮጀክቱ ውል በጊዜ፣ በበጀት፣ በጥራት እና በህጋዊ መስፈርቶች መሠረት እንዲፈጸም የሚያስተዳድር ቁልፍ ባለሙያ ነው።

​💡 ተመሳሳይ የሳይት ኢንጂነሪንግ መረጃዎችን ለማግኘት የፌስቡክ ገፃችን Follow ያድርጉ👇

https://www.facebook.com/profile.php?id=61592085774934

@etconp

Comments

Be the first to add a comment